በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩክሬን የሩሲያን የጸጥታው ም/ቤት ፕሬዚዳንትነት ተቃወመች


የዩክሬን ቀውስ አንድ ዓመት ያስቆጠረበት በተመድ ሲታሰብ
የዩክሬን ቀውስ አንድ ዓመት ያስቆጠረበት በተመድ ሲታሰብ

“የሩሲያ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ፕሬዚዳትነትን መረከብ ዓለም አቀፉን ማህበረሰብ በጥፊ እንደመምታት ነው” ሲሉ የዩክሬን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዲሚትሮ ኩሌባ ተናገሩ፡፡

ኩሌባ ይህን የተናገሩት፣ ሩሲያ በየወሩ የሚፈራረቀውን የተባበሩት መንግሥታትን፣ ከፍተኛ የደህንነት አካል ፕሬዚዳትነት፣ ትናንት ቅዳሜ ከተረከበች በኋላ ባስተላለፉት የትዊት መልዕክት ነው፡፡

ሞስኮ ይህን ኃላፊነት ለመጨረሻ ጊዜ የተረከበችው፣ ወታደሮችዋ ዩክሬን ላይ ሙሉ ወረራ በሰነዘሩበት እኤአ የካቲት 2022 እንደነበር ተመልክቷል፡፡

በተያያዘ ዜና ዩናይትድ ስቴትስ ለዩክሬን የአየር መከላከያ ራዳር፣ ጸረ ታንክ ሮኬቶች እና የነዳጅ ማጓጓዣ ቦቴዎችን ጨምሮ ለተለያዩ ወታደራዊ እርዳታዎች የሚውል የ2.6 ቢሊዮን ዶላር እርዳታ በሚቀጥለው ሳምንት ይፋ እንደምታደርግ የዩናይትድ ስቴትስ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የሩሲያው የመከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉም፣ በዩክሬን ለሚገኘው የሩሲያ ጦር የሚቀርቡ ተተኳሽ መሳሪያዎችን በከፍተኛ ደረጃ እንደሚጨምሩ የሩሲያን ጦር በጎበኙበት ወቅት ቃል መግባታቸውን፣ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ቴሌግራም ላይ ባስተላለፈው መልዕክት አመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG