በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

እስራኤል በሶሪያ በርካታ ይዞታዎችን ደበደበች


የእስራኤል ሮኬቶች በሶሪያ ካደረሱት ጥቃት
የእስራኤል ሮኬቶች በሶሪያ ካደረሱት ጥቃት

እስራኤል ዛሬ እሁድ ማለዳው ላይ በሶሪያ ሆምስ ግዛት በርካታ ስፍራዎች ላይ ባደረሰቸው የአየር ድብድባ አምስት ወታደሮች መቁሰላቸውን የሶሪያ መንግሥት ዜና ማሰራጫ ዘግቧል፡፡

ካለፈው ጥርና የአውሮፓውያኑ አዲስ ዓመት ወዲህ፣ እስራኤል ድብደባውን ስታካሂድ ለዘጠነኛ ጊዜ መሆኑን ጦርነቱን ከሚከታተሉ ተቃዋሚዎች ጋር ግንኙነት እንዳለው የተገለጸው በሶሪያ የሰብአዊ መብት ሁኔታዎች ተመልካች ቡድን አስታውቋል፡፡

ቡድኑ እስራኤል ወታደራዊ ይዞታዎችን እና የምርምር ማዕከላትን ጨምሮ፣ ከኢራን ጋር ግንኙነት ያላቸው ሚሊሻዎችን ኢላማ ያደረገ ጥቃት ማድረጓን አመልክቷል፡፡

እስራኤል በሆምስ ግዛትና አካባቢዎች ያሉ ይዞታዎችን ያጠቃች መሆኑን ያስታወቀው የሶሪያ የዜና አገልግሎት የሶሪያ መከላከያ አንዳንዶቹን ሚሳዬሎችን መትቶ መጣሉን አስታውቋል፡፡

በእስራኤል በኩል ስለ ድብደባው ወዲያውኑ የተሰጠ ምላሽ አለመኖሩን አሶሴይትድ ፕሬስ ዘግቧል፡፡

XS
SM
MD
LG