በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ ክልል ተከታታይ ድርቅ ያስከተለው ረኀብ ሰዎችንና እንስሳትን እየገደለ መኾኑ ተገለጸ


በደቡብ ክልል ተከታታይ ድርቅ ያስከተለው ረኀብ ሰዎችንና እንስሳትን እየገደለ መኾኑ ተገለጸ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:10 0:00

በደቡብ ክልል ተከታታይ ድርቅ ያስከተለው ረኀብ ሰዎችንና እንስሳትን እየገደለ መኾኑ ተገለጸ

• ከ337 ሺሕ በላይ ዜጎች የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ ይሻሉ


በኢትዮጵያ ደቡብ ክልል፣ ለድርቅ የተጋለጡ አርብቶ አደሮች፣ በቂ ሰብአዊ ርዳታ እንዳልቀረበላቸውና ከብቶቻቸውም እየሞቱባቸው እንደኾነ አስታወቁ። በምግብ እጥረት የተዳከሙት አርሶ አደሮቹ፣ ለበሽታ መጋለጣቸውንና አንዳንዶቹም በተያያዥ ጉዳቶች እየሞቱ መኾኑን ተናግረዋል። የክልሉ አርብቶ አደሮች ጉዳይ ቢሮ እንደገለጸው፣ ከ400ሺሕ በላይ አርብቶ አደሮች፣ በክልሉ ለተከታታይ ዓመታት ለዘለቀው ድርቅ ተጋላጭ መኾናቸውን ገልጿል። “በድርቁ ምክንያት የሞተ ሰው የለም፤” ያሉት የቢሮው ሓላፊ አቶ ሎሬ ካኩታ፣ ከ70ሺሕ በላይ ከብቶች መሞታቸውን አስታውቀዋል።

የአሜሪካ ድምፅ፣ ድርቁን በተመለከተ ከአነጋገራቸው የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ውስጥ አንዱ የኾኑት የሐመር ወረዳ ነዋሪ አቶ ኤምቡሌ ኬሎ፣ " ድርቁ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰብን ነው፤ ከብት እኮ የለም። በአጠቃላይ ወደ ስልሳ ከብት ነበረን፤ በከፊል አልቀዋል፤ 15 ብቻ ይቀረናል። እነርሱም በአስጊ ኹኔታ ውስጥ ናቸው። አራት ከብቶች አሁንም ከተኙበት አይነሡም። ይተርፋሉ ብዬ አልገምትም። መኖ ቢኖርም፣ ውሃ ግን የለም። መኖው ተበልቶ ውኃ ሲጠጣ ነው ለሕይወት የሚበጀው።" ብለዋል።

በደቡብ ኦሞ ዞን፣ ከ465 ሺሕ በላይ አርብቶ አደሮች መኖራቸውን የጠቀሱት የክልሉ አርብቶ አደሮች ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ አቶ ሎረ ካኩታ፣ ለዓመታት ዘልቋል ላሉት ድርቅ መጋለጣቸውንና ብዙዎቹ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ ለመጠበቅ መገደዳቸውን ገልጸዋል። የድርቁን ጉዳት ለመቀነስ፣ ከብቶቹን ወደ ሌላ ስፍራ ለማጓጓዝ ጥረት ቢደረግም፣ የመንግሥት ችግር ተዘጋጅቶ አለመጠበቅ እንደኾነ አስረድተዋል፡፡

"በየወረዳው፣ ከ70 ሺሕ ኩንታል በላይ የሚይዙ ጎተራዎችን ገንብተናል። በዚኽ አራት ዓመት ትልቁ ችግር ተዘጋጅቶ አለመጠበቅ ነው። በርግጥ የሀብት እጥረትም አለ። የቀጣይ ዓመት ዕቅዶች ከወዲኹ ጸድቀው፣ ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ችግሮች በደንብ እንዘጋጃለን፡፡"

በየወረዳው፣ ከ70 ሺሕ ኩንታል በላይ የሚይዙ ጎተራዎችን ገንብተናል። በዚኽ አራት ዓመት ትልቁ ችግር ተዘጋጅቶ አለመጠበቅ ነው። በርግጥ የሀብት እጥረትም አለ። የቀጣይ ዓመት ዕቅዶች ከወዲኹ ጸድቀው፣ ሊያጋጥሙ ለሚችሉ ችግሮች በደንብ እንዘጋጃለን፡፡"


በደቡብ ኦሞ ዞን ዝናም የጠፋው፣ ከ2012 ዓ.ም. ጀምሮ ባሉት ዓመታት ነው፡፡ ይህን ተከትሎ፣ ከ337 ሺሕ በላይ ዜጎች፣ የአስቸኳይ ጊዜ የምግብ ርዳታ እንደሚያሻቸው ቪኦኤ ያነጋገራቸው የደቡብ ኦሞ ግብርና መምሪያ ሓላፊ አቶ ባንከ ሱሜ ገልጸዋል።

በድርቁ ምክንያት ምርት በመጥፋቱ፣ ሰዎች እና እንስሳት ለምግብ እጥረት እና ለረኀብ መጋለጣቸውን፤ አንዳንዶቹም በዚኹ ሳቢያ እንዲሁም በተያያዥ በሽታ ለኅልፈት መዳረጋቸውን ተናግረዋል።

"የአርብቶ አደሩ መታወቂያው ከብቱ ነው። አሁን ከብቶቹ የሉም፤ እንዳሉ ሞተው አልቀዋል። የሚበላም የሚጠጣም በማጣት፣ ወደ 16 ሰዎች ናቸው የሞቱት። እገሌ በምን ምክንያት ሞተ ሲባል በድርቅ እየተባለ ነው፡፡" ያሉ ሲኾን ፣ የክልሉ አርብቶ አደሮች ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ አቶ ሎረ ካኩታ፣ "በድርቁ ምክንያት የሞተ ሰው የለም" በማለት ያስተባብላሉ።

"የአርብቶ አደሩ መታወቂያው ከብቱ ነው። አሁን ከብቶቹ የሉም፤ እንዳሉ ሞተው አልቀዋል። የሚበላም የሚጠጣም በማጣት፣ ወደ 16 ሰዎች ናቸው የሞቱት። እገሌ በምን ምክንያት ሞተ ሲባል በድርቅ እየተባለ ነው፡፡"


ከእናቶች እና ሕፃናት ጋራ በተያያዘ ችግሮች ነበሩ። በተለይ፣ በጤና ኬላዎች ተኝተው የሚታከሙ አይተናል። እውነት ለመናገር፣ እንደ ክልል፣ እስከ አሁን ድረስ የተመዘገበ ሞት የለም፡፡

ኾኖም፣ የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ዶክተር ተስፋየሱስ ተፈራ፣ “በድርቁ ምክንያት ተርቦ የሞተ ሰው የለም ማለት አይቻልም፤” ሲሉ፣ የአርብቶ አደሮች ጉዳይ ቢሮ ሓላፊውን ርግጠኝነት በማስረጃ ይቃወማሉ፡፡

በምግብ እጥረት የተጎዱ በየወሩ በአማካይ ከ40 በላይ ሕፃናት በሆስፒታሉ ተኝተው እንደሚታከሙ የጠቀሱት ሜዲካል ዳይሬክተሩ፣ ሕይወታቸው ያለፉ መኖራቸውንም ተናግረዋል።

የክልሉ አርብቶ አደሮች ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አቶ ሎረ ካኩታ፣ የተከታታይ ዓመታት ድርቅ በአስከተለው ረኀብ፣ ከ70ሺሕ በላይ ከብቶች መሞታቸውን አረጋግጠዋል። የአስቸኳይ ርዳታ ሰጪ አካላትን እገዛንም ጠይቀዋል።

የአርብቶ አደር አካባቢ ቆላማ ነው። ለአራት ተከታታይ ዓመታት፣ በድርቅ ውስጥ ነው ያለነው። የአገራችን ሕዝብ፣ ለእነዚኽ አካባቢዎች ከፍ ያለ ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪዬን ማስተላለፍ እፈልጋለኹ።

አርብቶ አደሮችን ጨምሮ በክልሉ፣ ከሦስት ሚሊዮን በላይ ዜጎች የምግብ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋቸው፣ የክልሉን ባለሥልጣናት ጠቅሰን መዘገባችን ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG