በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

36 የህወሓት አመራሮች ከእስር ተፈቱ


ዛሬ ከእስር ከተፈቱት መካከል የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈጉባዔ ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ይገኙበታል
ዛሬ ከእስር ከተፈቱት መካከል የቀድሞ የኢትዮጵያ ፌዴሬሽን ምክር ቤት የቀድሞ አፈጉባዔ ወ/ሮ ኬርያ ኢብራሂም ይገኙበታል

በወንጀል ተጠርጥረው ክሥ ቀርቦባቸው የነበሩ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክሥ፣ ማቋረጡን የፍትሕ ሚኒስቴር ከአስታወቀ በኋላ፣
36 ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ ከእስር መለቀቃቸውን ጠበቆቻቸው ተናገሩ።

ዛሬ ከእስር ከተፈቱት ከፍተኛ የህወሓት አመራሮች መካከል፥ ወይዘሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ ዶ/ር ዐዲስዓለም ባሌማ እና ዶ/ር አብርሃም ተከሥተ እንደሚገኙበት ከጠበቆቻቸው አንዱ አቶ ሀፍቶም ከሠተ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

ከእስር ተፈቺዎቹ፣ በማረሚያ ቤት መኪኖች፥ ሳሪስ፣ ፒያሳ እና ሲኤምሲ ወደሚገኙ ቤተ ሰዎቻቸው እንደተሸኙና ቤተ ሰዎቻቸወም አቀባበል እንደ አደረጉላቸው አቶ ሃፍቶም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በዛሬው ዕለት ከእስር የተፈቱት 16ቱ የህወሓት የሲቪል እና ወታደራዊ ባለሥልጣናት፣ ላለፉት ኹለት ዓመታት በዶ/ር ደብረ ጽዮን ገብረ ሚካኤል የክሥ መዝገብ ሥር እንደነበሩ ጠበቃው አውስተዋል።

በሌተናል ጀነራል ታደሰ ወረደ የክሥ መዝገብ ሥር ጉዳያቸው በፍርድ ቤት ሲታይ የቆየው 20 ተከሣሾች እንደኾኑም ጠበቃው ጠቅሰዋል፡፡

“በወንጀል ተጠርጥረው ክሥ ቀርቦባቸው የነበሩ፣ የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮችን ክሥ በማቋረጥ፣ ጉዳያቸው በቀጣይ በሽግግር ፍትሕ ማኅቀፍ እንዲታይ ማድረግ አስፈላጊ ኾኖ ተገኝቷል፤” ሲል የፍትሕ ሚኒስቴር በፌስቡክ ገጹ ላይ በአሰፈረው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የተከሣሽ ሲቪል እና ወታደራዊ አመራሮቹ ጉዳይ፣ በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ችሎት ሲታይ መቆየቱ ይታወሳል፡፡

XS
SM
MD
LG