በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራሲን ለማስፋፋት ተጨማሪ 690 ሚሊየን ዶላር ቃል ገባች


ዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራሲን ለማስፋፋት ተጨማሪ 690 ሚሊየን ዶላር ቃል ገባች
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:10 0:00

ዩናይትድ ስቴትስ ዲሞክራሲን ለማስፋፋት ተጨማሪ 690 ሚሊየን ዶላር ቃል ገባች

ዩናይትድስቴትስ ዲሞክራሲን በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚያስፋፉ ፕሮግራሞችን ለማበረታታት አዲስ የገንዘብ ድጋፍ እንደምታደርግ አስታውቃለች። የዩክሬን ፕሬዚዳንትም ረቡዕ እለት በዋሽንግትን የሚካሄደው የዲሞክራሲ ጉባዔ ላይ በርቀት በድህረገፅ አማካኝነት ተገኝተው ገለፃ አድርገዋል።

በዩናይትድ ስቴትስ ዋሽንግተን እየተካሄደ ባለው የዲሞክራሲ ጉባዔ ሁለተኛ ቀን ስብሰባ ላይ የተገኙት የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዥ፣ የዲሞክራሲ እሴቶች፣ የህግ የበላይነት እና የሰብዓዊ መብቶች መከበር በዓለም ዙሪያ ጥቃት እየደረሰባቸው መሆኑን ገልፀው "ሰዎች በነፃነት እንዲደራጁ፣ እንዲሳተፉ እና እንዲወያዩ የሚያስችሉ መድረኮች እየጠበቡ፣ ህገመንግስታዊ መብቶች እየተገደቡ እና የዜጎች ነፃነት እየተሸረሸረ ነው። ሀሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በፍጥነት እየወደቀ ነው" ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ጉተሬዥ ሀገሮች በድጋሚ መተማመንን እንዲገነቡ እና አለመመጣጠንን እንዲቀርፉ ጥሪ ባቀረቡበት ወቅት፣ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ደግሞ ዲሞክራሲን የሚያስፋፉ በርካታ ፕሮግራሞችን እንደሚደግፉ አስታውቀዋል።

"በሚቀጥሉት ሁለት ዓመታት ፕሬዚዳንታዊ ተነሳሽነቱ ላይ ሌላ ተጨማሪ 690 ሚሊየን ዶላር የመጨመር እቅድ አለን። በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ ደግሞ በዓለም ዙሪያ ዲሞክራሲን ለማስፋፋት ለምናደርገው ጥረት 9.5 ሚሊየን ዶላር ለመመደብ የኔ አስተዳደር ከምክርቤቱ ጋር አብሮ ለመሥራት አስቧል።"

ፕሬዚዳንቱ አክለው ዲሞክራሲያዊ አስተዳደርን ለሚያራምድ ቴክኖሎጂ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ ገልፀዋል። "በዚህ ሳምንት መጀመሪያ እዚህ ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ፣ መንግስት አሜሪካ ውስጥ ጨምሮ በመላው ዓለም የሚገኙ ተቃዋሚዎችን፣ የመብት አቀንቃኞችን እና ጋዜጠኞችን ኢላማ ለማድረግ ጥቅም ላይ ሲውል የነበረውን፣ ገበያ ላይ የዋለ የስለላ መሳሪያ መጠቀምን የሚከለክል ትዕዛዝ ፈርሜያለሁ። " ብለዋል።

የዩክሬን መከላከያ ሚኒስቴር ወታደሮቻቸው ጀርመን ያቀረበቻቸውን የትጥቅ መኪናዎች ለሙከራ ሲነዱ የሚያሳይ ምስል ትላንት አውጥቶ አውጥቶ ነበር። በዋሽንግተን እየተደረገ ባለው ጉብዔ ላይ ደግሞ በድህረገፅ አማካኝነት የተገኙት የዩክሬን ፕሬዚዳንት ቮለድሚር ዘለንስኪ የሩሲያን ወረራ በመቃወም ሀገራቸውን መደገፉ ለምን ወሳኝ እንደሆነ ዓለምን አስታውሰዋል።

"ሩሲያ ከዓለም ዲሞክራሲያዊ ሀገሮች ጋር፣ ከሁላችሁም ጋር ለረጅም ጊዜ ጦርነት ውስጥ ቆይታለች። በሐሰተኛ ምረጃ፣ በምርጫ ጣልቃ ገብነት፣ በስለላ፣ በሙስና፣ በሳይበር ወንጀሎች ትዋጋለች።"

ዘለንስኪ አክለው በዚህ አመት የዩክሬንን ድል ሊያረጋግጥ የሚችል ተጨማሪ የጦር መሳሪያ ድጋፍ እንዲደረግላቸውም ጠይቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ፣ በሞስኮ፣ የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ ከኢራኑ አቻቸው ሆሴን አሚር-አብዱላሂ ጋር ተገናኝተው በታህራን የሽምግልና ጥረቶች ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን አሚር-አብዱላሂ "ስለ ዩክሬን ተወያይተናል። ውጊያውን የሚያስቆም ማንኛውንም ተነሳሽነት እንደግፋለን" ብለዋል።

በዩክሬን የሚገኘውን ዛፖሪዢአ የተሰኘውን የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ጣቢያ የጎበኙት የዓለም አቀፉ የአቶሚክ ኃይል ኤጀንሲ ሃላፊ ራፋኤል ማሪያኖ ግሮሲም እንዲሁ ኪየቭ እና ሞስኮ ውይይታቸውን እንዲያፋጥኑ አሳስበዋል።

/ቬሮኒካ ባልደራስ ኤግሌሲያስ ያጠናቀረችውን ዘገባ ስመኝሽ የቆየ ወደ አማርኛ መልሳዋለች/

XS
SM
MD
LG