በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የ40 ዓመቱ የዳላስ ማኅበረሰብ ማዕከል እና መጪው የእግር ኳስ ስፖርት


የ40 ዓመቱ የዳላስ ማኅበረሰብ ማዕከል እና መጪው የእግር ኳስ ስፖርት
please wait

No media source currently available

0:00 0:15:35 0:00

በዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ግዛት ዳላስ ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያዊያን ማኅበረሰብ ማዕከል፣ በስፍራው ለሚኖረው ትውልደ ኢትዮጵያዊ ማኅበረሰብ ነፃ የሕክምና አገልግሎት የሚሰጥ አዲስ ክሊኒክ በማቋቋም ላይ መኾኑን አስታወቀ።

ድርጅቱ፣ በመጪው ዓመት፣ በቴክሳስ ዳላስ ፎርትዝ ለሚካሔደው 40ኛው የሰሜን አሜሪካ ኢትዮጵያዊያን ስፖርት ፌዴሬሽን በዓል ለመሳተፍ ዝግጅት በማድረግ ላይ እንደኾነ፣ የማዕከሉ ፕሬዝዳንት ወ/ሮ አዲስ ጥበቡ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

የቤት ግዥ እና ሽያጭ(የሪል ስቴትስ ኤጀንት) ባለሞያ የኾኑት ወ/ሮ አዲስ፣ የማኅበረሰብ ማዕከሉ፣ “40 ዓመታትን አስቆጥሮ ኹለተኛው ትውልድ እየተረከበው ነው፤” ይላሉ፡፡ የማኅበረሰብ ማዕከሉ በመስጠት ላይ ስለሚገኘው የተለያዩ ማኅበራዊ ግልጋሎቶችም አብራርተዋል፡፡

XS
SM
MD
LG