በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በትግራይ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር ዓረና ተቃወመው


በትግራይ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር ዓረና ተቃወመው
please wait

No media source currently available

0:00 0:03:25 0:00

“በአሁኑ ጊዜ በትግራይ ክልል እየተቋቋመ ያለው ጊዜያዊ አስተዳደር፣ ፍትሕንና ዴሞክራሲን ሊያረጋገጥ አይችልም፤” ሲል ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲ እና ለሉዓላዊነት ፓርቲ ገለጸ::

ፓርቲው በአወጣው መግለጫ፣ በክልሉ ኹሉን ያካተተ እና ወደ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ የሚያሸጋግር ጊዜያዊ አስተዳደር መቋቋም አለበት፤ ብሏል::

ፓርቲው አያይዞም፣ በህወሓት እና የትግራይ ኀይሎች የሚመራ ጊዜያዊ አስተዳደር የሚያቋቁመው ኮሚቴ፣ አግባብነት የሌለውን ወታደራዊ ተቋም በፖለቲካ የሚያስገባ ኢ-ሕገ መንግሥታዊ ነው፤ በማለት ተቃውሞታል::

የፓርቲው የሕዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ዓምዶም ገብረ ሥላሴ፣ የሰላም ስምምነት ከተፈረመ ወዲህ አምስተኛ ወሩን ሊያስቆጥር መኾኑን ጠቁመው፣ እስከ አሁን ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሳይቋቋም መቆየቱ አግባብነት የለውም፤ ብለዋል፡፡

የትግራይ ችግር እጅግ ውስብስብ እና ከባድ ነው፤ ያለው ይኸው የዓረና መግለጫ፤ በመቶ ሺሕዎች የሚቆጠሩ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው፣ የተፈናቀሉ እና ረዳት አልባ የኾኑ ቤተሰቦች፣ በሠቆቃ ውስጥ በአሉበት በዚኽ ወቅት፣ ችግሩ በአንድ እና ቅቡልነቱን በዕጣ ፓርቲ አመራር ይፈታል የሚል እምነት የለንም፤ ሲል አቋሙን ገልጿል፡፡

XS
SM
MD
LG