በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ካማላ ሃሪስ ከጋና ፕሬዚዳንት ጋራ ተወያይተዋል


ጋና በጉብኝት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ  ከአገሪቱ ፕሬዚደንት ናና አኩፎ አዶ  ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል
ጋና በጉብኝት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ  ከአገሪቱ ፕሬዚደንት ናና አኩፎ አዶ  ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል

ጋና በጉብኝት ላይ የሚገኙት የዩናይትድ ስቴትስ ምክትል ፕሬዚደንት ካማላ ሃሪስ ከአገሪቱ ፕሬዚደንት ናና አኩፎ አዶ ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል፡፡ ውይይታቸው ኢኮኖሚያዊ እና አካባቢያዊ ጸጥታን ጨምሮ በበርካታ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ መሆኑ ተመልክቷል፡፡

ዛሬ ምሽት ፕሬዚደንት አኩፎ አዶ እና ባለቤታቸው ቀዳማዊት እመቤት ሬቤካ አኩፎ ለምክትል ፕሬዚደንት ሃሪስ እና አብረዋቸው ለተጓዙት ባለቤታቸው ደግ ኢምሆፍ ባዘጋጁት የእራት ግብዣ አድርገዋል። በግብዣው ላይም ዩናይትድ ስቴትስ የሚኖሩ አፍሪካውያንን ጨምሮ ከሦስት መቶ በላይ እንግዶች እንደተጋበዙ ቀደም ብሎ የወጣው መረጃ አመልክቷል፡፡

ዩናይትድ ስቴትሷ ምክትል ፕሬዚደንት ወጣት ሙዚቀኞች ባለሞያዎች የሚገለገሉበትን ቫይብሬት ስፔስ የተባለ የማኅበረሰብ ስቱዲዮ እንደሚጎበኙ ተጠቁሟል፡፡ በጉብኝታቸው ላይ የፊልም ተዋናይ ኢድሪስ ኤልባ እና ሼሪል ሊ ራልፍ አብረዋቸው እንደሚገኙ እና ከሙዚቃ ባለሞያዎች ጋር እንደሚተዋወቁ የወጣው የጉብኝታቸው የጊዜ ሰሌዳ ያሳያል፡፡

ነገ ማክሰኞ ደግሞ ምክትል ፕሬዚደንት ሃሪስ በባርነት የተገዙ አፍሪካውያን በመርከብ እየተጫኑ ወደአሜሪካ በተጋዙበት ለሁለቱም ሀገሮች አስከፊ ጠባሳ በተወው የባሪያ ንግድ መናሃሪያ ኬፕ ኮስት ካስል ንግግር ያደርጋሉ፡፡

ካማላ ሀሪስ ተነገ ወዲያ ረቡዕ በንግድ ስራ ከተሰማሩ ሴቶች ጋር የሚገናኙ ሲሆን ባለቤታቸው ደግ ኢምሆፍ ደግሞ ሁለት ሴቶች የከፈቱትን የቸኮላት ፋብሪካ ይጎበኛሉ፡፡ ረቡዕ ማታ ወደ ታንዜኒያ ይጓዛሉ፡፡

XS
SM
MD
LG