በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ትረምፕ በቴክሳስ ባደረጉት የምርጫ ዘመቻ የቀረበባቸውን ክስ አጣጣሉ


የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በ2017 ዓ.ም. (የዛሬ ሁለት ዓመት) ለሚደረገው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር የመጀመሪያ ዘመቻቸውን ቅዳሜ መጋቢት 16/2015 ዓ.ም በቴክሳስ ግዛት ዋስኮ ከተማ አካሂደዋል።
የቀድሞ የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትረምፕ በ2017 ዓ.ም. (የዛሬ ሁለት ዓመት) ለሚደረገው የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ለመወዳደር የመጀመሪያ ዘመቻቸውን ቅዳሜ መጋቢት 16/2015 ዓ.ም በቴክሳስ ግዛት ዋስኮ ከተማ አካሂደዋል።

በእምቢተኛነታቸውና ቀስቃሽ ንግግሮችን በማድረግ የሚታወቁት እና ከፊታቸው ክስ የሚጠብቃቸው ዶናልድ ትረምፕ በ2017 ዓ.ም. (የዛሬ ሁለት ዓመት) በሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ ለመወዳደር የመጀመሪያ ዘመቻቸውን ቅዳሜ በቴክሳስ ግዛት ዋስኮ ከተማ አካሂደዋል። ከተማዋ ለሰዎች ሞት ምክንያት የሆነ በሕግ አስከባሪዎች ላይ የተደረገ ተቃውሞ በማስተናገድ ትታወቃለች።

ትረምፕ ዘመቻቸውን የከፈቱት ባልተለመደ መልኩ ጥር 6፣ 2021 ዓ.ም በአሜሪካ ምክርቤት ላይ በተነሳው አመፅ በነበራቸው ሚና ለእስር የተዳረጉ ሰዎች ብሄራዊ መዝሙር ሲዘምሩ የሚሰማበትን 'ፍትህ ለሁሉም' የተሰኘ ዘፈን በማጫወት እና ትረምፕ የታማኝነት ቃለመሃላ ሲያነቡ የተቀረፀ ድምፅ በማሰማት ነበር። በምክርቤቱ የነበረውን አመፅ የሚያሳዩ ምስሎችም በስክሪኖች ላይ ታይተዋል።

ትረምፕ ባደረጉት ቁጭት የተሞላበት የመክፈቻ ንግግር በአመፁ የተሳተፉ ሰዎችን ደግፈው ተከላክለዋል፣ በቀድሞው የሪፐብሊካን ፕሬዚዳንት ላይ የሚካሄዱ ምርመራዎችን የሚከታተሉ ዐቃቢያነ ሕግን በቁጣ ነቅፈዋል። እየተካሄዱ ያሉ ምርመራዎችንም በእርሳቸው እና በተከታዮቻቸው ላይ ላይ እየተፈፀመ እንዳለ የፖለቲካ ጥቃት አድርገው አሳይተዋል።

"በጣም ያልተለመደ ነገር ነው እየተካሄደ ያለው" ያሉት ትረምፕ "የሕግ ባለሞያዎች የሚያዩትን ማመን አይችሉም። ከ11 ሚሊየን ገፅ በላይ ያላቸውን የመረጃ ሰነዶች ነው እየተመለከቱ ያሉት። እኔ ትልቅ ተቋም ነው የገነባሁት። 11 ሚሊየን ገፅ ውስጥ ምንም ሊያገኙ አይችሉም። በዛ ላይ ግብር የከፈልኩበት ማስረጃዎች አሉ። ያ እንደውም በሀገራችን ታሪክ እጅግ ንፁሁ ሰው እንድሆን ያደርገኛል። ጓደኞቼ ያንን ነው የሚሉት።" ብለዋል።

ትረምፕ አክለው "ነፃ ትወጣላችሁ ትኮራላችሁ" ሲሉ እሳችቸውም ሆኑ ተከታዮቻቸው ከክስ ነፃ እንደሚወጡ አስረግጠው ተናግረዋል። "የፍትህ ሥርዓታችንን እያበላሹ ያሉት ዘራፊዎች እና ወንጀለኞች ይሸነፋሉ፣ ተዓማኒነታቸውን ያጣሉ፣ እናም ይዋረዳሉ።" ብለዋል።

ትረምፕ ቅዳሜ እለት ይፋ ያደረጉት ይህ የምርጫ ዘመቻ ተቃዋሚዎችን ያበረታታ እና የቀድሞው ፕሬዚዳንት በዩናይትድ ስቴትስ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በወንጀል ቢከሰሱ ሁከት ሊፈጠር ይችላል የሚለውን ግምት ከፍ ያደረገ ነው።

ትረምፕ ይህን የምርጫ ዘመቻ ጨምሮ ከቅርብ ግዜ ወዲህ ባደረጓቸው ንግግሮች የተጠቀሙባቸው ቋንቋዎች፣ ከዚህ ቀደም በተካሄደው ምርጫ ላሸነፉት የዲሞክራቱ ተፎካካሪ ጆ ባይደን የስልጣን ሽግግር እንዳይደረግ ለማድረግ የሞከሩ ደጋፊዎቻቸው የአሜሪካ ምክር ቤት ህንፃ ላይ ወረራ ከማድረጋቸው በፊት የተጠቀሙበትን ቋንቋ ያስተጋባ ነው።

ትረምፕ በቅዳሜው ንግግራቸው "ጠላቶቻችን ሊያስቆሙን በጣም ይፈልጋሉ" ያሉ ሲሆን "ተቃዋሚዎቻችን መንፈሳችንን ለመጨፍለቅ እና ፍላጎታችንን ለመስበር የሚችሉትን ሁሉ አድርገዋል" ብለዋል።

አክለውም "ግን አልተሳካላቸውም" ያሉት ትረምፕ "እንደውም የበለጠ እንድንጠነክር አድርገውናል፣ የ2024ቱ ምርጫ የመጨርሻው ጦርነት ነው፣ ትልቅ ነው የሚሆነው። እናንተ ዋይት ኋውስ መልሳችሁ አስቀምጡኝ፣ የሥልጣን ዘመናቸው ያበቃና አሜሪካ እንደገና ነፃ ሀገር ትሆናለች።" ብለዋል።

XS
SM
MD
LG