በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የራያ የማንነት ጥያቄ ምላሽ ያግኝ የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ


የራያ የማንነት ጥያቄ ምላሽ ያግኝ የሚል ሰላማዊ ሰልፍ ተካሄደ
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:18 0:00

ከማንነት ጋር ተያይዘው ለሚነሱ ጥያቄዎች መንግሥት አፋጣኝ ምላሽ እንዲሰጥ የሚጠይቅ ሰላማዊ ሰልፍ ትናንት በአላማጣ ከተማ ተካሄደ።

የአሜሪካ ድምፅ በስልክ ያነጋገራቸው ሰልፈኞቹ በሰጡት አስተያየት፤ ሥልጣናቸውን የተጠቀሙ ፖለቲከኞች ነጥቀውብናል ያሉትን ማንነት ዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ እንዲገነዘብ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ይህንን ሰልፍ በተመለከተ የትግራይ ክልል ኮምዩኒኬሽን ቢሮ ዛሬ ባወጣው መግለጫ፤ “ትናንት መጋቢት 10/ 2015 ዓ.ም ከጉባ ላፍቶ፣ ወልድያ እና ቆቦ ወረዳዎች ጨምሮ ከተለያዩ አማራ ክልል ከተሞች አካባቢዎች ብዙ ሕዝብ በማመላለስ በአላማጣ ከተማ ተቀባይነት የሌለው ሰልፍ ተካሂዷል።”ብሏል።

“የሰላም ሂደቱ ወደተሻለ አቅጣጫ እየሄደ ባለበትና በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር እየተመሰረተ ባለበት በዚህ ጊዜ፤ ደቡብ ትግራይ ውስጥ ሰላማዊ ሕዝብን የሚያውክ በደል እየተፈፀመ ነው። ሰላማዊ ሰዎች ላይም ከፍተኛ ግፍ ተፈጽሟል” ያለው መግለጫው “ይህ ተግባርም የኢትዮጵያ መንግሥት ሊያስቆመው ይገባል” ሲልም የፌዴራሉን መንግሥት ጣልቃ ገብነት ጠይቋል።

ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG