በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ታንዛንያ ለሞዛምቢክ አውሎ ነፋስ ተጎጂዎች ዕርዳታ ላከች


ፎቶ ኤ.ኤፍ.ፒ (03.18.2023)
ፎቶ ኤ.ኤፍ.ፒ (03.18.2023)

ታንዛኒያ ፍሬዲ በተባለው ከባድ ዝናብና አውሎ ነፋስ ለተጎዱ በሺዎች ለሚቆጠሩ ሰዎች የሚውል የምግብ እና የነፍስ አድን ምግብ ማቆያ መሳሪያዎችን ለጎረቤት አገሯ ሞዛምቢክ ልካለች፡፡

በአደጋው ከ190 በላይ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረና 584 የሚሆኑ ሰዎች ሲጎዱ 37 የሚሆኑት የደረሱበት እንዳልታወቀ ተነግሯል፡፡

የሠራዊቱ ተጠባባቂ የመረጃ ዲሬክተር በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት 1ሺ ሜትሪክ ቶን ዱቄት፣ 6ሺ ብርድ ልብስና 50 ድንኳኖች እንዲሁም ሁለት ሄሊኮፕተሮች ወደ ሞዛምቢክ እንደተላከ ተናግረዋል።

37 የሚሆኑ ዕቃ ጫኝ ተሽከርካሪዎች ዕርዳታውን ለማድረስ እንደተመደቡም ዲሬክተሩ ጨምረው ገልጸዋል።

በሞዛምቢክ ያለው ሁኔታ ፈታኝ እንደሆነና ከታናዛኒያ የተገኘው ዕርዳታ አስቸኳይ ምላሽ ለሚሹ ችግሮች እንደሚውል ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG