በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በእስራኤል የመንግስት ተቃዋሚዎችና ደጋፊዎች ሰልፍ ወጡ


በእስራኤል ባለፈው ሳምንት የተካሄደው ተቃውሞ (ፎቶ አሶስዬትድ ፕረስ)
በእስራኤል ባለፈው ሳምንት የተካሄደው ተቃውሞ (ፎቶ አሶስዬትድ ፕረስ)

ለእስራኤል የፍትህ ማሻሻያ የቀረበውን ሃሳብ ተንተርሶ ሁለቱም ወገኖች ማለትም የመንግስቱ ደጋፊዎች እና ተቃዋሚዎች የሆኑ በሺዎች የሚቆጠሩ ዜጎች ትላንት ወደ ቴል አቪቭ ጎዳናዎች መውጣታቸውን ተከትሎ ፖሊስ ማንኛውንም የኃይል ግጭት ለማስወገድ ጣልቃ መግባቱ ተዘገበ።

ከመንግስት ደጋፊዎች፣ አንዳንዶቹ ማንነታቸው እንዳይታወቅ ጭምብል አጥልቀው የመንግስትን ተቃዋሚዎች ሲሳደቡ ተስተውለዋል።

የጠቅላይ ሚንስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ መንግስት የህግ ማሻሻያውን እያካሄደ ባለበት በአሁኑ ወቅት ተቃዋሚዎች ጠቅላይ ፍርድ ቤቱን ያዳክማል እንዲሁም የሀገሪቱን መሰረታዊ ነፃነቶች አደጋ ላይ ይጥላል በሚል የተቀሰቀሰው ቀውስ 11ኛ ሳምንቱን ይዟል።

ተቃዋሚዎች ኔታንያሁ የክስ ሂደት ላይ ሳሉ የሕግ ማሻሻያ ለማድረግ መሞከራቸውንም ይጋጫል ሲሉ ተችተዋል።

XS
SM
MD
LG