በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮሪያ በሣምንት ውስጥ ሶስተኛውን ሚሳዬል አስወነጨፈች


ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ያሰወነጨፈችው ሚሳዬል (ፎቶ ሮይተርስ)
ሰሜን ኮሪያ ዛሬ ያሰወነጨፈችው ሚሳዬል (ፎቶ ሮይተርስ)

ሰሜን ኮሪያ የአጭር ርቀት ባሊስቲክ ሚሳዬል ዛሬ ማለዳ ወደ ባህር አስወንጭፋለች። ይህም አሜሪካና ደቡብ ኮርያ ለሚያደርጉት ወታደራዊ እንቅስቃሴ ምላሽ ነው ተብሏል።

የደቡብ ኮሪያ ኤታማዦር ሹም እንዳሉት ዛሬ ማለዳ የተወነጨፈው ሚሳዬል በአገሪቱ ሰማይ ላይ አልፎ በምሥራቅ በሚገኘው የውሃ አካል ላይ አርፏል።

ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ የጦር ልምምድ ከጀመሩ ካለፈው ሳምንት ወዲህ ሰሜን ኮሪያ ሚሳዬል ስታስወነጭፍ ሶስተኛው መሆኑ ነው።

ሰሜን ኮርያ ልምምዶቹን የምትመልከተው እንደ ወረራ ልምምድ ነው ሲል አሶስዬትድ ፕረስ በዘገባው አመልክቷል።

ደቡብ ኮሪያ አሜሪካና ጃፓን የሚሳዬሉን መወንጨፍ አውግዘው፣ የአካባቢውን ሰላም ለማወክ የሚደረግ ጥረት ነው ብለዋል።

XS
SM
MD
LG