የህወሓት ቃል አቀባይ አቶ ጌታቸው ረዳ በትግራይ ክልል በመቋቋም ላይ የሚገኘውን የክልሉን ጊዜያዊ አስተዳደር በፕሬዚዳንትነት እንዲመሩ ከህወሓት በኩል መታጨታቸውን ለፓርቲው ቅርበት ያላቸው ምንጮች ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።
ዓለም አቀፍ የትግራይ ምሑራን ማኅበር ሌተናል ጄነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን የክልሉ ምክትል ፕሬዚዳንት እንዲሆኑ ባለፈው ሳምንት በእጩነት ማቅረቡ ይታወቃል::
የአቶ ጌታቸውና ሌሎች የጊዜያዊ አስተዳደሩ ካቢኒ ኣባላት ሹመት፣ የክልሉ አመራሮች ከፌደራሉ መንግሥት ጋር በጊዜያዊ አስተዳደሩ አወቃቀር ጉዳይ ተወያይተው ካፀደቁት በኋላ አስተዳደሩ ሥራ እንደሚጀምር ምንጮቻችን ጨምረው ገልፀዋል።