በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ከአሜሪካ ጋር እስረኛ ልቀያየር ነው ማለቷን ዩናይትድ ስቴትስ አጣጣለች


የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሒያን
የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆሴን አሚራብዶላሒያን

አንድ ከፍተኛ የኢራን ዲፕሎማት ‘ከዩናይትድ ስቴትስ ጋር እስረኛ የመለዋወጥ ስምምነት ላይ ተደርሷል’ ሲሉ ተናገሩ። ይሁን እንጂ ንግግራቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ አላቀረቡም። ዩናይትድ ስቴትስም ይህን ንግግራቸውን “ጨካኝ ውሸት” በሚል አጣጥላዋለች።

ሚኒስቴሩ ከዚህ ቀደም ዩናይትድ ስቴትስ ባገደቻቸው ንብረቶች ላይ ተመሳሳይ አስተያየት ቢሰጡም ምንም ፍሬ ሳይታይ ቆርቷል።

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሆሴን አሚራብዶላሒያን በኢራን የመንግስት ቴሌቪዥን ላይ ቀርበው “በቅርቡ እስረኛ ለመቀያየር በዩናይትድ ስቴተስ እና በኢራን መሃከል ስምምነት ተደርሷል” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “በዩናይትድ ስቴትስ በኩል ሁሉም ነገር እንደታሰበው ከሄደ የእስረኛ ልውውጡ በአጭር ጊዜ ውስጥ ይፈጸማል” ብለዋል።

አሶሺየትድ ፕሬስ የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒቴር ቃል አቀባይ ኔድ ፕራይስን በጉዳዩ ላይ አስተያየት እንዲሰጡ የጋበዘ ሲሆን፤ ቃል አቀባዩ የሚንስቴሩን አስተያየት “በቤተሰቦች መከራ ላይ ተጨማሪ የሚሆን ሌላ ክፉ ውሸት” ሲሉ አስተያየቱን ተችተዋል።

ኔድ ፕራይስ “በኢራን በስህተት የታሰሩትን ሦስት አሜሪካዊያንን ለማስፈታት ያለመታከት እየሰራን ነው” ያሉ ሲሆን አያይዘውም “እነዚህ ሰዎች ከሚወዷቸው ጋር ካልተገናኙ በስተቀር ጥረታችንን አናቆምም” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG