በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሶማሊያ ፓርላማ የመምሪያ ምክር ቤት አዲስ ጸረ ሽብርተኛ ህግ አጸደቀ


የሶማሊያ ፓርላማ የመምሪያ ምክር ቤት ትናንት ረቡዕ አዲስ ጸረ ሽብርተኛ አጸደቀ፡፡
የሶማሊያ ፓርላማ የመምሪያ ምክር ቤት ትናንት ረቡዕ አዲስ ጸረ ሽብርተኛ አጸደቀ፡፡

የሶማሊያ ፓርላማ የመምሪያ ምክር ቤት ትናንት ረቡዕ አዲስ ጸረ ሽብርተኛ አጸደቀ፡፡ ህጉ የሶማሊያ መንግሥት የጸጥታ ተቋማት ሽብርተኝነትን በተሻለ መንገድ ለማስወገድ የሚረዳቸው የህግ መዋቅር እንዲኖር የታለመ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ህጉ በ133 አባላት ድጋፍ የጸደቀ ሲሆን 3 አባላት ተቃውመዋል፡፡ ሰባት አባላት ድምጸ ተአቅቦ አድርገዋል፡፡

የሶማሊያ መንግሥት የደህንነት ዋና ዳይሬክተር የሶማሊያ ፀጥታ እንዲሻሻል ወሳኝ እንደሆነ በገለጹት ህግ ትናንት ረቡዕ የጸደቀው የምክር ቤት አባላቱ ለበርካታ ሳምንታት ክርክር ካካሄዱ በኋላ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ ሶማሊያ ውስጥ ባለሥልጣናትን በመግደል እና ሰሜን ምስራቃዊዋ ፑንትላንድ የሽብርተኛ ጥቃት በፈጸም የተፈረደባቸው 13 የአልሻባብ ታጣቂዎች የሞት ቅጣት እንደተፈጸመባቸው ተገለጠ፡፡ የአልሻባብ አባላቱ በተለያዩ የፑንትላንድ ከተሞች ተረሽነዋል ሲሉ የሶማሊያ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል፡፡

የፑንትላንድ የጦር ፍርድ ቤት ሊቀመንበር አብዲፈታህ አደም ለቪኦኤ በሰጡት ቃል ፍርድ ቤቱ በ13ቱ ተከሳሾች ላይ እአአ ከ2017 እስከ 2022 በነበረው ጊዜ የሞት ቅጣት ውሳኔ ያስተላለፈባቸው ናቸው፡፡

XS
SM
MD
LG