በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ከመምሕርነት ወደ መንገድ ላይ ንግድ


please wait

No media source currently available

0:00 0:06:44 0:00

ታስተምርበት ከነበረው አክሱም ዩኒቨርስቲ በጦርነቱ ምክኒያት የወር ደሞዟ በመቋረጡ ከመምሕርነት ወደ መንገድ ላይ ንግድ የገባችው ወጣት የዛሬው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን እንግዳችን ናት።

ደሞዝ ከተቋረጠ በኋላ ገቢ እንዳልነበራትና ገቢ ለማግኘት ያገኘችው ሥራ የጉልት በመሆኑ እሱን መሥራት እንደጀመረች የምትናገረው ብርሃን ወልደገብርኤል የሦስት ዓመት ልጇን ለመመገብ የመንገድ ላይ ንግድ መጀመሯን ትገልፃለች።

“ይህም ቢሆን ሥራ ነው” ያለችን ብርሃን የተማረችው ችግር በሚያጋጥም ግዜ እንዴት ተቋቁማ ማለፍ እንዳለባትም ጭምር ለመረዳት መሆኑን ተናግራለች። “ትምሕርት በግል የሚደርስብህን ችግር ለመፍታት ካልጠቀመህ ምንም ዋጋ የለውም” ብላናለች።

ብርሃን በጋዜጠኝነትና ኮምዩኑኬሽን ትምሕርት የመጀመሪያ ዲግሪዋን ከመቐለ ዩኒቨርሲቲ ሁለተኛውን ደግሞ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተቀብላለች።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG