በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች ተገደሉ


በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ አካባቢ በተቀሰቀሰ ግጭት ሰዎች ተገደሉ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:05 0:00

በኦሮሚያና ሲዳማ ክልል አዋሳኝ በሚገኙ ጉቦሄማና ቦጨሣ በተባሉ አከባቢዎች በተከሰተ ግጭት 12 ሰዎች መገደላቸውን የተጎጂ ቤተሰቦች መሆናቸውን የገለፁ ነዋሪዎች ተናገሩ።

በጉዳዩ ላይ ከአካባቢው ባለሥልጣናት መረጃን ለማግኘት ያደረግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። በሌላ በኩል የጭሪ ወረዳ ጤና ጣቢያ ባለሞያ በጥይት ቆስለው ጤና ጣቢያ ለደረሱ ሰዎች የሕክምና አገልግሎት መስጠታቸውና ተጨማሪ ሕክምና ያስፈልጋቸዋል ያሉትን ደግሞ ወደ ከፍተኛ ሆስፒታል መላካቸውን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ሐዋሳ ቅርንጫፍ ስለ ጉዳዩ መረጃ እንዳላቸው ጠቅሶ በቅርቡ ሪፖርት ይፋ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

ሙሉውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።

XS
SM
MD
LG