በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ዩክሬን የሚገኙ የሩሲያ ወታደሮች ጎበኙ


ይህ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር የሚዲያ አገልግሎት ከለቀቀው የቪዲዮ ምስል ላይ የተወሰደ ፎቶ መከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጊ ሾይጉ ዩክሬን ውስጥ ትክክለኛ ስፍራው ባልተገለፀ ስፍራ ለሩሲያ ወታደሮች ንግግር ሲያደርጉ ያሳይል።
ይህ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር የሚዲያ አገልግሎት ከለቀቀው የቪዲዮ ምስል ላይ የተወሰደ ፎቶ መከላከያ ሚኒስትሩ ሰርጊ ሾይጉ ዩክሬን ውስጥ ትክክለኛ ስፍራው ባልተገለፀ ስፍራ ለሩሲያ ወታደሮች ንግግር ሲያደርጉ ያሳይል።

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስትር ሰርጌ ሾይጉ በደቡብ ዶኔትስክ አቅጣጫ ምስራቃዊ ወታደራዊ ወረዳ የሚገኘውን እዝ መጎበኝታቸውን መስሪያ ቤታቸው ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

ከዩክሬን ጋር እያደረገችው ባለው ጦርነት ሩሲያ ባሳየችው ደካማ ተሳትፎ ሾይጉ የሚወቀሱ ሲሆን ቅዳሜ እለት ይፋ የወጣ ምስል መከላከያ ሚኒስትሩ ለሩሲያ መከላከያ ሀይሎች ሜዳሊያ ሲሰጡ አሳይቷል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ አንድ አመት ያስቆጠረው ሩሲያ በዩክሬን ላይ ያደረገችው ወረራ በሀገሪቱ ምስራቃዊ ክልሎች ወደሚደረግ የእግረኛ ጦርነት መሸጋገሩን የእንግሊዝ መከላከያ ሚኒስትር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል። ለዚህም ምክንያቱ የሞስኮ ኃይሎች የመድፍ ጥይት እጥረት ስላጋጠማቸው ነው ብሏል።


ሚኒስትር መስሪያ ቤቱ በቅርቡ ባካሄደው ዳሰሳ በዩክሬን ውስጥ በቅርብ ርቀት የሚደረጉ ውጊያዎች እየጨመሩ መሄዳቸውን አንዳንድ መረጃዎች ይሳያሉ ብሏል። መስሪያ ቤቱ ባለፈው ወር ሩሲያ ተጠባባቂ ወታደሮቿን ማሰማራቷን አስታውቆ የነበረ ሲሆን የዩክሬንን ጠንካራ ቦታ ጥይት እና አካፋ ብቻ ታጥቀው እንዲያጠቁ መታዘዛቸውን ተናግረው ነበር።

የዩክሬን ፕሬዝዳንት ቮለድሚር ዚለንስኪ በእለታዊ መግለጫቸው ከተለያዩ አካላት ጋር ስብሰባዎችን እና ድርድሮችን እያካሄዱ መሆናቸው ገልፀው ዋና ትኩረታቸው ደክሞ ሩሲያን ለድርጊቷቿ ተጠያቂ ማድረግ መሆኑን አስታውቀዋል።

XS
SM
MD
LG