በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የናይጄሪያ ጠ/ፍ/ቤት አሮጌዎቹ የገንዘብ ኖቶች እንዲቆዩ አዘዘ


ናይጄሪያ ውስጥ ሰዎች ከባንክ ፊት ለፊት ሲጠባበቁ እኤአ የካቲት 22 2023 (ፎቶ ፋይል)
.
ናይጄሪያ ውስጥ ሰዎች ከባንክ ፊት ለፊት ሲጠባበቁ እኤአ የካቲት 22 2023 (ፎቶ ፋይል) .

የናይጄሪያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የአገሪቱ መንግሥት አዲሱ ያወጣው የገንዘብ ኖት ለውጥ ህገ መንግሥታዊ አይደለም ሲል ነባሮቹ የገንዘብ ኖቶች እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ ጥቅም ላይ እንዲቆዩ አዟል፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ትናትን ዓርብ ያስተላለፈው ውሳኔ የናይጄሪያ ክፍለ ግዛት አገረ ገዥዎች ነባሮቹ የባለ 200፣ 500 እና 1ሺ የገንዘብ ኖቶች (naira) ለረጅም ጊዜ እንዲቆዩ የካቲት 9 ቀን 2015 ዓም የመሰረቱትን ክስ ተመልክቶ መሆኑን ተነግሯል፡፡

የናይጄሪያ መንግሥት ባለፈው የአውሮፓውያኑ ዓመት አዲስ የገንዘብ ኖቶችን ማውጣቱን ገልጾ ናይጄሪያዊያን በስድስት ሳምንታት ውስጥ ወደ አዳዲሶቹ የገንዘብ ኖቶች እንዲቀይሯቸው አዞ ነበር፡፡

ወደ ኋላውም ላይ ቀነ ገደቡ ለ10 ቀናት የተራዘመ ቢሆንም ባንኮች ግን ባለፈው ወር መጨረሻ ላይ የገንዘብ ኖቶቹን መቀበል ማቆማቸው ተመልክቷል፡፡

የናይጄሪያ ባለሥልጣናት የገንዘብ ኖቶቹን መቀየር ያስፈለገው በገበያው ላይ ያለውን ትርፍ የገንዘብ መጠን ለመቆጣጠር፣ ወንጀልንና አፈናን ለመዋጋት፣ እንዲሁም የዋጋ ግሽበትና ሀሰተኛ ወንጀለኞችን ለመከላከል መሆኑን ይናገራሉ፡፡

ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ ግን በፕሬዚዳንት ሙሃሙዱ ቡሃሪ የተደገፈው ፖሊሲ ህገ መንግሥታዊ ያልሆነውን የአስፈጻሚውን ሥልጣን የሚያመለከት፣ የገንዘብ ችግር ያለባቸውና ለህልውናቸው በፈጣን የንግድ ልውውጥ የሚተዳደሩ ናይጄሪያዊያን ዜጎችን መሰረታዊ መብቶች የሚጥስ ነው በሚል ውድቅ ያደረገው መሆኑን ተመልክቷል፡፡

XS
SM
MD
LG