በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሌ - አሜሪካውያን የሶማሌላንድ ግጭት እንዲያበቃ ጠየቁ


ሶማሌ አሜሪካውያን አርብ የካቲት 24/2015 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ደጃፍ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።
ሶማሌ አሜሪካውያን አርብ የካቲት 24/2015 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ደጃፍ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ለጉዳዩ ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።

ከሶማሊያ ተገንጥላ በምትገኘው አወዛጋቢዋ ሶማሌላንድ ውስጥ በሠራዊቱ አባላትና በታጣቂዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ከ100 በላይ ሰዎች መሞታቸውንና 500 መቁሰላቸውን ተከትሎ ጦርነቱ እንዲያበቃ የሚጠይቁ ሶማሌ አሜሪካውያን ዋሽንግተን ዲሲ ውስጥ ሰልፍ አደረጉ።
ከተለያዩ የዩናይትድ ስቴትስ ግዛቶች የተውጣጡ ወደ 200 የሚጠጉ ሶማሌ አሜሪካውያን አርብ የካቲት 24/2015 ዓ.ም በዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ደጃፍ ባደረጉት ሰላማዊ ሰልፍ ለጉዳዩ ተገቢው ትኩረት እንዲሰጠው ጠይቀዋል።
የአካባቢው ሚሊሺያዎች ሦስት ክልሎችን ከሶማሌ ላንድ ለመነጠል ውጊያ ማድረግ ከጀመሩ ሳምንታት ተቆጥረዋል። እስካሁን የተደረጉ የተኩስ አቁም ጥሪዎች ችላ ተብለው ውጊያው እንደቀጠለ ነው።
የሶማሊያን ባንዲራ ይዘው ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ ደጃፍ ሰልፍ ያካሄዱት ሰልፈኞቹ ፤ በሱል ዋና ከተማ ላስኖድ በተካሄደው ጦርነት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች በመደገፍ ጦርነቱን የሚቃወሙ መፈክሮችን ሲያሰሙ ተደምጠዋል።
የሶማሌ ላንድ ፕሬዚዳንት ሙሴ ቢሂ የሚቃወሙና ፕሬዚዳንቱ ከሥልጣን እንዲወርዱ የሚጠይቁ መፈክሮችን አሰምተዋል። ላሳኖድ ውስጥ እየተካሄደ ያለው ጦርነት ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲቆም ጠይቀዋል።
ይህንን ግጭት ሸሽተው ወደ ኢትዮጵያ የገቡ ሶማሌያዊያን ስደተኞች ቁጥር 83 ሺህ መድረሱን የኢትዮጵያ የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት እና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የስደተኞች ጉዳይ ከፍተኛ ኮሚሽን ከቀናት በፊት ባወጡት የጋራ መግለጫ ማስታወቃቸው ይታወሳል።

XS
SM
MD
LG