በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በካሜሩንና ኒጀር በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች ዕርዳታ ይሻሉ


ፎቶ ፋይል (ኤ.ኤፍ.ፒ)
ፎቶ ፋይል (ኤ.ኤፍ.ፒ)

በቦኮ ሃራም ቁጥጥር ስር የነበሩትና በካሜሩንና ኒጀር የሚገኙ በርካታ አካባቢዎች የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በረሃብ፣ በጎርፍና በሰደድ እሳት እየተንገላቱ እንደሆነ የሁለቱ አገሮች ባለሥልጣናት በመናገር ላይ ናቸው።

የእርሻ መሬታቸው በጎርፍና በሰደድ እሳት የወደመባቸው በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የነፍስ አድን ዕርዳታ እንደሚያሰፈልጋቸው ባለሥልጣናቱ ተናግረዋል።

ግጭትን በመሸሽ ቀያቸውን ለቀው የነበሩ አሁን በመመለስ ላይ በመሆናቸው መልሶ ለማስፈርና ኑሯቸውን እንደገና ለማስጀመር ዕርዳታ ይሻሉ ተብሏል።

በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው ቦኮ ሃራም ለ 36 ሺህ ሰዎች ሞት ተጠያቂ ሲሆን፣ 3 ሚሊዮን የሚሆኑት ደግሞ መኖሪያቸውን ጥለው ለመፈናቀል ተገደዋል ሲል የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታውቋል።

የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) እንደሚለው፣ በምዕራብና ማዕከላዊ አፍሪካ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል። ከፍተኛ የሆነ የገንዘብ ዕጥረት እንደገጠመው የሚያወሳው ቢሮው 7.4 ሚልዮን የሚሆኑ ተረጂዎችን ለመታደግ 2.53 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስፈልገው አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG