በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በሶማሊላንድ ውጊያው እንደቀጠለ ነው


ላስ-አኖድ በተባለው የሶማሊላንድ ሪፐብሊክ ውጊያው እየጋመ መምጣቱንና ባለፉት ሶስት ሳምንታት ከ100 በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ከሕክምና ሰጪዎች የተገኘው መረጃ ያመለክታል።

ከ 30 ዓመታት በፊት ከሶማሊያ ተገንጥላ ራሷን በምታስተዳድረው ሶማሊላንድ ያሉ ሚሊሺያዎች ሶስት ክልሎችን ገንጥለው ወደ ሶማሊያ መልሰው ለመቀላቀል በመዋጋት ላይ ናቸው።

ተደጋግሞ የተደረገው የተኩስ ማቆም ጥሪ ሰሚ አላገኘም።

የሶማሊላንድ ሠራዊት ከሚሊሺያዎቹ ጋር ላለፉት ሶስት ሳምንታት ውጊያ ሲያካሂድ ቆይቷል።

ላስ-አኖድ፣ ሳናግ እና ካይን የተባሉት ክልሎች ከሶማሊላንድ ተገንጥለው ወደ ሶማሊያ መልሰው ለመቀላቀል እየተዋጉ መሆኑን የቪኦኤው አህመድ ሞሃመድ ዘገባ ያመለክታል።

በውጊያው 105 ሰዎች ሲሞቱ፣ 602 ደግሞ መቁሰላቸውን የአካባቢ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል።

በድርቅ ሳቢያ ቀድሞውንም ችግር ላይ ባለው አካባቢ ጦርነት መታከሉ እጅግ አሳሳቢ ነው ሲሉ የረድኤት ድርጅቶች በመናገር ላይ ናቸው።

XS
SM
MD
LG