በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኬንያ በተቀበረ ፈንጂ ሶስት ፖሊሶች ተገደሉ


በሰሜን ምሥራቅ ኬንያ በአል-ሻባብ ሳይፈጸም እንዳልቀረ በተጠረጠረና በፖሊስ መኪና ላይ በተከፈተ ጥቃት ሁለት ፖሊሶች ሲገደሉ ሶስት ሌሎች መቁሰላቸውን የጸጥታ ባለስልጣናት አስታውቀዋል።

የፖሊስ ተሽከርካሪው ዳዳብ በተሰኘ የስደተኞች መጠለያ አቅራቢያ በተቀበረ ፈንጂ ላይ ሲወጣ አደጋው መድረሱ ታውቋል።

የአካባቢው የጸጥታ ባለስልጣናት ለቪኦኤ አስተያየት ባይሰጡም፣ አንድ የፓርላማ አባል ግን መንግስት አል-ሻባብን ለመከላከል የሚጠቀምበትን ዘዴ እንዲቀይር ጠይቀዋል።

ባለፈው ሳምንትም በተመሳሳይ መንገድ የድንበር ጠባቂ ፖሊሶች መኪና የተቀበረ ፈንጂ ሲረግጥ ሶስት ፖሊሶች ሕይወታቸውን አጥተዋል።

XS
SM
MD
LG