በተለምዶ አጠራሩ "አሜሪካን ግቢ" እየተባለ በሚታወቀው የአዲስ አበባ ሠፈር የሚገኘው እና የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ መኖሪያ ኾኖ ያገለገለው ቤት፣ የጥንት ይዞታውንና ቅርጹን በጠበቀ አኳኋን ጥገና ተደርጎለት ተመረቀ።
የዳግማዊ ንጉሠ ነገሥት ዐፄ ምኒልክ የጦር ሚኒስትር የነበሩት እና በምክር ዐዋቂነታቸው እና በአመራር ፈሊጣቸው "አባ መላ" በመባል የሚታወቁት ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ መኖሪያ ቤት፣ በወራሪው ፋሽስት ኢጣልያ ዘመን፣ ከ700 ያላነሱ ኢትዮጵያውያን ሕይወት ከእልቂት የተረፈበት ሥፍራ እንደኾነም አንድ የታሪክ ተመራማሪ ተናግረዋል።
የዘገባውን ሙሉ ይዘት ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ።