በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል


ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:10:04 0:00

በኢትዮጵያ ለ6ኛ ተከታታይ ወቅት ዝናብ ላይጥል እንደሚችል በመገመቱ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል ሲል አክሽን አጌንስት ሀንገር የተሰኘው በአፍሪካ ቀንድ ረሃብን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ተቋም አስጠነቀቀ። እስካሁን በኢትዮጵያ ቢያንስ 12 ሚሊየን ሰዎች ለሞት ለሚዳርግ የድርቅ አደጋ መጋለጣቸውን እና ከ4.5 ሚሊየን በላይ የቀንድ ከብቶች መሞታቸውንም የተቋሙ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቤዛ አበበ ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ለ6ኛ ተከታታይ ወቅት ዝናብ ላይጥል እንደሚችል በመገመቱ ደቡብ እና ደቡብ ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍሎች ለረሃብ አደጋ ተጋልጠዋል ሲል አክሽን አጌንስት ሀንገር የተሰኘው በአፍሪካ ቀንድ ረሃብን ለማጥፋት የሚንቀሳቀሰው ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ ርዳታ ሰጪ ተቋም አስጠነቀቀ።

እስካሁን በኢትዮጵያ ቢያንስ 12 ሚሊየን ሰዎች ለሞት ለሚዳርግ የድርቅ አደጋ መጋለጣቸውን እና ከ4.5 ሚሊየን በላይ የቀንድ ከብቶች መሞታቸውን የገለፁት የተቋሙ የኢትዮጵያ ፕሮግራም ዳይሬክተር ቤዛ አበበ፣ ለከፋ የተመጣጠነ ምግብ እጥረት የተጋለጡ ህፃናት ቁጥርም በከፍተኛ ሁኔታ እየጨምረ መሄዳቸውን አመልክተዋል። በአዲስ አበባ እየተካሄደ ያለው የአፍሪካ ህብረት ስብሰባ በቀጠናው እየከፋ የሄደውን ድርቅ ለመቅረፍ ቅድሚያ ሰጥቶ እንዲወያይም ጠይቀዋል።

XS
SM
MD
LG