በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢንተርኔት አማካኝነት ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች


በኢንተርኔት አማካኝነት ሴቶች ላይ የሚፈፀሙ ጥቃቶች
please wait

No media source currently available

0:00 0:09:59 0:00

በ128 ሀገሮች ውስጥ ለሴቶች እና ልጃገረዶች መብት ተሟጋች በሆኑ ሴቶች ጥምረት የተመሰረተው እና 'Every Women Treaty' ወይም 'የሁሉም ሴቶች ስምምነት' የተሰኘው ተቋም ባለፈው ሳምንት ያወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው፣ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ሴቶች 73 ከመቶ የሚሆኑት አንድ ወይም ከዛ በላይ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደርስ ጥቃት ይደርስባቸዋል። እነዚህ ጥቃቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያክል ይፈፀማሉ? በሴቶች ላይ የሚያደርሱት ጉዳትስ ምን ይመስላል?

በኢንተርኔት አማካኝነት ሴቶች ላይ የሚደርስ ጥቃት እጅግ በጣም እየተስፋፋ የመጣ ፆታዊ ጥቃት መሆኑን በርካታ ጥናቶች ያመለክታሉ።
ለምሳሌ በ128 ሀገሮች ውስጥ ለሴቶች እና ልጃገረዶች መብት ተሟጋች በሆኑ ሴቶች ጥምረት የተመሰረተው እና 'Every Women Treaty' ወይም 'የሁሉም ሴቶች ስምምነት' የተሰኘው ተቋም ባለፈው ሳምንት ያወጣው ሪፖርት እንዳመለከተው፣ በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ ሴቶች 73 ከመቶ የሚሆኑት አንድ ወይም ከዛ በላይ በኢንተርኔት አማካኝነት የሚደርስ ጥቃት ይደርስባቸዋል።
ከነዚህ ጥቃቶች መካከልም ኮምፒውተር እና ተንቀሳቃሽ ስልክ የመሳሰሉ የኤሌክትሮኒክስ መገናኛዎችን በመጠቀም የሚፈፀሙ ተደጋጋሚ ማስፈራራቶች ወይም ማዋከቦች፣ የጥላቻ ንግግሮች፣ ወሲባዊ ጥቃቶች፣ የመደፈር ዛቻዎች እና የተጋለጡ እና እርቃን የፎቶ ምስሎችን እንዲሁም ቪዲዮዎችን ያለፈቃዳቸው ማሰራጨት ይገኙበታል።
እነዚህ ጥቃቶች በኢትዮጵያ ውስጥ ምን ያክል ይፈፀማሉ? በሴቶች ላይ የሚያደርሱት ጉዳትስ ምን ይመስላል ስትል ስመኝሽ የቆየ በኢንተርኔት አጠቃቀም ደህነት ዙሪያ ጥናቶችን ያጠናችውን እና ግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናዎችን የምትሰጠውን ሰላማዊት ተዘራን አነጋግራታለች።
XS
SM
MD
LG