በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናገሩ


የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናገሩ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:28 0:00

የደቡብ ኦሞ ዞን ነዋሪዎች ለረሃብ መጋለጣቸውን ተናገሩ

ለተከታታይ አራት ዓመታት በተከሰተ ድርቅ ምክኒያት በደቡብ ክልል በተለይ ደቡብ ኦሞ ዞን በመቶ ሺሆች የሚቆጠሩ ዜጎች ለረሃብ መጋለጣቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ። በቂ እርዳታ እንደማይሰጣቸውም ገልፀዋል።

ከድርቁ ጋራ በተያያዘ በተከሰቱ በሽታዎች የህፃናት ሕይወት ማለፉንም ነዋሪዎቹ ገልጸዋል። በየወሩ ከ40 በላይ ህፃናት ህክምና በመከታተል ላይ መሆናቸውን የገለፁት የጂንካ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር ሕይወታቸው ያለፉም መኖራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል።

የዞኑ ግብርና መምሪያ ከ337 በላይ ዜጎች አስቸኳይ ጊዜ የምግብ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው ገልጿል። የክልሉ ባለሥልጣናት በአከባቢው ቅኝት እያደረጉ ሲሆን የደቡብ ክልል አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን ለመንግሥት መገናኛ ብዙኃን ከስፍራው በሰጠው መገለጫ በክልሉ ቆላማ አካባቢዎች ከፍተኛ የሆነ የዝናብ እጥረት በመከሰቱ በሰብል ላይ ጉዳት መድረሱንና የምግብ እጥረት መከሰቱን አስታውቋል።

/ዝርዝሩን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG