በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በደቡብ አፍሪካ ሁለት ተሽከርካሪዎች ተጋጭተው 20 ሰዎች ሞቱ


ፋይል - በደቡብ አፍሪካ የመኪና አደጋ
ፋይል - በደቡብ አፍሪካ የመኪና አደጋ

ሊምፖፖ በተሰኘው የደቡብ አፍሪካ አውራጃ በትናንትናው ዕለት አንድ የሰዎች ማጓጓዣ አውቶብስ ከገንዘብ አመላላሽ ተሽከርካሪ ጋር ተጋጭቶ 20 ሰዎች ወዲያውኑ ሲሞቱ 60 የሚሆኑት ደግሞ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ገንዘብ አመላላሹ ተሽከርካሪ መንገዱን ሲስት ከአውቶብሱ ጋር ፊት ለፊት በመላተሙ አደጋው ሊደርስ መቻሉን የአካባቢው የትራንስፖርት መምሪያ አስታውቋል።

ከተጎጂዎቹ መካከል አስር የሚሆኑት ከፍተኛ ጉዳት የደረሰባቸው በመሆኑ ወደ ሆስፒታል የተወሰዱ ሲሆን ሌሎች ሰዎች በአካባቢው ባለ ወንዝ ሰምጠው እንደሁ ለማጣራት የፖሊስ ባህር ጠላቂዎች ወንዙን እያሰሱ ናቸው።

የአደጋው መንስኤ አሁንም በመጣራት ላይ ሲሆን ሰሞኑን የሚጥለው ከፍተኛ ዝናብ አካባቢውን እያጥለቀለቀ መሆኑን ባለሥልጣናት ለኤ.ኤፍ.ፒ የዜና ወኪል ተናግረዋል።

XS
SM
MD
LG