በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በፈረንሣይ የቀጠለው ተቃውሞ


በፓሪስ ዛሬ ከተካሄደው ተቃውሞ የተወሰደ (ፎቶ ሮይተርስ የካቲት 11, 2023)
በፓሪስ ዛሬ ከተካሄደው ተቃውሞ የተወሰደ (ፎቶ ሮይተርስ የካቲት 11, 2023)

የጡረታ ዕድሜ ከ62 ወደ 64 መራዘሙንና ሌሎች ጡረታን የተመለከቱ ጥቅማጥቅሞችን በተመለከተ መንግስት ሊያወጣ ያሰበውን አዲስ ህግ በመቃወም በመቶ ሺህ የሚቆጠሩ ፈረንሣውያን በመላ አገሪቱ አውራ ጎዳናዎችን አጨናንቀው ውለዋል።

ከሌሎች የበለጸጉ አገሮች አንጻር ሲታይ ፈረንሣዮች በርካታ ዓመታትን በጡረታ የማሳለፍ መብት ሲኖራቸው፣ የሕዝብ አስተያየት ጥናቶች እንደሚያሳዩት ይህን መብት በቀላሉ አሳልፉ ለመስጠት ፈረሣዮቹ ፈቃደኞች አይደሉም።

ፕሬዝደንት ኢማኑኤል ማክሮን በበኩላቸው የጡረታ ህጉን ማሻሻል ለጡረታ ሥርዓቱ ቀጣይነት ወሳኝ ነው።

የተቃውሞ ሰልፉን የሚያስተባብሩት የሠራተኛ ማኅበራት ባለፈው ወር ከአንድ ሚሊዮን ሰዎች በላይ ተቃውሞ የወጡበትን ሰልፍ ለመድገም ወይም ከዚያም ቁጥር በላይ ያላቸው ሰልፈኞችን ለማሳተፍ እየሠሩ ነው።

ማኅበራቱ ባወጡት የጋራ መግለጫ መንግስት የጡረታ ህጉን መቀየሩን እንዲያቆም ጠይቀዋል። “ካልሆነ ግን በሚቀጥለው ወር ፈረንሣይን ቀጥ እናደርጋታለን” ሲሉ ዝተዋል።

በመጪው ሐሙስ የሥራ ማቆም አድማ መጠራቱንም የሮይተርስ ዘገባ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG