በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ሪፖርቶች ጠቆሙ


ከኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት የተገኘ
ከኢኦተቤ መገናኛ ብዙኀን አገልግሎት ሥርጭት ድርጅት የተገኘ

ደቡብ ኢትዮጵያ ውስጥ በምትገኝ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያን፤ ላይ ቅዳሜ ዕለት በተፈፀመ ጥቃት ሦስት ሰዎች መገደላቸውን ኃይማኖታዊ ብዙኃን መገናኛ ዘግበዋል።

በጥንታዊቷ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ውጥረቱ የተፈጠረው ከሲኖዶሱ የወጡ ሦስት ጳጳሳት የጵጵስና ሹመት ሰጥተው በኢትዮጵያ የኦሮሚያ እና የብሔር ብሔረሰቦች ቅዱስ ሲኖዶስ በሚል ተገንጣይ ሲኖዶስ በማቋቋማቸው ነው።

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ሄኖክ በኦሮሚያ ክልል ሻሸመኔ ከተማ የተፈፀመውን ድርጊት “አሳፋሪና ልብ ሰባሪ” ማለታቸውን ተዋኅዶ ሚዲያ ማዕከል የተባለው ኃይማኖታዊ ሚዲያ ዘግቦታል።

አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ ይህንን ሚዲያ ጠቅሶ እንደዘገበው፤ ሻሸመኔ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል ጥቃት በመፈፀም ሁለት ወጣቶችን ሲገድ ሌሎች አራት ወጣቶችን ደግሞ አቁስሏል ብሏል።

በኋላም ቤተክርቲያኒቱ አካባቢ ከሚገኝ ትልቅ ሕንፃ ላይ ከአልሞ ተኳሽ በተነጣጠረ ጥቃት አንዲት ሴት ስትገደል ሌሎች ደግሞ ቆስለዋል። መረጃውን ከሌላ ተጨማሪ አካል ማረጋገጥ እንዳልቻለ ኤኤፍፒ በዘገባው ጠቅሷል። አቡነ ሄኖክ የኦሮሚያ ክልል ባለሥልጣናት በኦርቶዶክስ ክርስቲያን አማኞች ላይ የሚደርሰውን ማሳደድ እንዲያስቆሙ መጠየቃቸውን የተዋህዶ ሚዲያው ዘግቧል።

በሌላ በኩል የኢትዮጵያ ቅዱስ ሲኖዶስ “አዋጅ” ሲል ባወጣም መግለጫ በሀገር ውስጥ እና ከሀገር ውጭ የሚገኙ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ካህናት እና ምእመናን ጥቁር ለብሰው የካቲት አምስት ቀን ሰላማዊ ተቃውሞ እንዲያደርጉ ጥሪ አስተላልፏል። በዛሬ ዕለት አዲስ አበባ የሚገኙ አብዛኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያት በሕንፃዎቻቸው ፊት ላይ ላይ የሐዘን መግለጫ ምልክት የሆነ ጥቁር ጨርቅ ሰቅለው ታይተዋል።

ከ115 ሚሊዮን ከሚገመተው የኢትዮጵያ ሕዝብ 40 በመቶውን የሚሸፍነውና በዓለም ላይ ካሉት አንጋፋዎቹ አንዱ የሆነው የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አንድነት ያፈነገጠው ቡድን በወሰደው እርምጃ ስጋት ላይ መውደቁን ኤኤፒ ዘገቧል።

ላለፉት አስርት ዓመታት በፓትርያርክ አቡነ ማቲያስ የምትመራው ቤተክርስቲያን ከሲኖዱሱ ተገንጥለው ሌላ ሲኖዶስ ያቋቋሙትን ጳጳሳት ከስልጣናቸው በማገድ ድርጊቱም ሕገ ነው ስትል በይፋ አውግዛለች። በተጨማሪም የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ በጉዳዩ ላይ ጣልቃ ገብተው ቤተክርስቲያኒቷ ሕገ ወጥ ላለችው ቡድን እውቅና የሚሰጥ አስተያየት መስጠታቸውን ቤተክርስቲያኒቷ ተቃውማለች።

በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ ለካቢኔ አባሎቻቸው ማብራሪያ የሰጡት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አሕመድ ሁለቱም ወገኖች የራሳቸው እውነት ስላላቸው ቀርበው እንዲነጋገሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ከሲኖዶሱ ያፈነገጡት ጳጳሳት “በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ ሞመናን በቋንቋቸው አይገለገሉም።እንዲሁም አድሎና የበላይነት አለ” ሲሉ ቤተክርስቲያኗን ይወቅሳሉ። ይህ ወቀሳ በፓትርያርኩ ውድቅ ተደርጓል።
የኦርቶዶክስ መሪዎች ከዓመታት በፊት የተቃጠሉ ቤተከርስቲያናትን ጨምሮ በአምነቱ ተካታዮች ላይ ይደረጋል በሚሉት ጫና ቅሬታቸውን ሲገልፁ ቆይተዋል። በተጨማሪን የትግራይን ግጭት ጨምሮ በቤተክርስቲያኒቱ እና በመንግሥት መካከል ያለው ውጥረት ነግሷል።
የዓለም የቤተክርስቲያን ምክርቤት በኢትዮጵያ የተፈጠረው ሁኔታ እጅግ እንደሚያሳስበው ገልፆ አርብ ዕለት መግለጫ አውጥቷል።
የምክር ቤቱ ዋና ፀሐፊ ጄሪ ፕሌይ “በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም የፖለቲካ መሪዎች በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አባላቷ መካከል አንድነትና ሰላም ለማስፈን የምታደርገውን ጥረት እንድትደግፉ እንጠይቃለን።” ብለዋል።

XS
SM
MD
LG