በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የቅዱስ ሲኖዶሱ መልስ እና የዋሺንግተን ዲሲው ሰልፍ


በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታዮች ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አከናውነዋል ።
በዋሺንግተን ዲሲ እና አካባቢው የሚኖሩ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነት ተከታዮች ከዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አከናውነዋል ።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ በሰሞኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የሹመትውዝግብ ጉዳይ የሰጡትን ማብራሪያ እና መንግሥታቸው የወሰደውን አቋም ተቃወመ፤ አስቸኳይ የእርምት ርምጃ የማይወስዱ ከኾነም፣ በቅዱስ ፓትርያርኩ እና በብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት የሚመራ፣ በቤተ ክርስቲያኒቷ ላይ እየተፈጸመ ነው ያሉትን በደል ለዓለም አቀፉ ኅብረተሰብ የሚያሰማ ሰላማዊ ሰልፍ እንደሚጠራ አስጠነቀቀ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ፣ ትላንት ለሚኒስትሮች ካቢኔ አባሎቻቸው በሰጡት የወቅታዊ ጉዳይ ማብራሪያ ላይ፣ በቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ እና ሕገ ወጥ ሢመት ፈጽመዋል በተባሉ አባቶች መካከል ስለተቀሰቀሰው ውዝግብ አንሥተው ሲያብራርይ፣ጉዳዩ ቀላል እንደኾነ ጠቅሰው፣ኹለቱ ቡድኖች እየጦዘ የመጣውን አለመግባባት በንግግር እንዲፈቱት ጠይቀዋል።

በሌላ ዜና፣ ከዚኹ ጉዳይ ጋራ በተያያዘ በዋሽንግተን ዲሲ የሚገኙ የእምነቱ አባቶች፣ አገልጋዮች እና ምእመናን፣ የመንግሥትን ጣልቃ ገብነት በግልጽ ያረጋገጠ ነው፤ ያሉትን የጠቅላይ ሚኒስትሩን ማብራሪያ እና መንግሥታቸው እያሳየ ነው ያሉትን አድሏዊ አቋም በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ አካሒደዋል።

የቤተ ክርስቲያንን ሃይማኖታዊ ሕግጋትና ቀኖና የሚያፋልስ ሊቀ ጳጳስ /ኤጲስ ቆጶስ/ ሹመት ሰጥተዋል ከተባሉ የኮሚቴ አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ በዛሬው የሲኖዶሱ መግለጫ ላይ ያላቸውን አስተያየት ለማካተት ያደርግነው ተደጋጋሚ ሙከራ አልተሳካም። ምላሻቸው እንዳገኘን ይዘን እንመለሳለን።

XS
SM
MD
LG