በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ወደ መቶ ፍልስተኛ የያዘችው ኦሸን ቫይኪንግ ጣልያን ወደብ ደረሰች


ዘጠና ስድስት ፍልስተኞችን ያሳፈረችው ኦሺን ቫይኪንግ የምትባል ነፍስ አድን መርከብ ማዕከላዊ ሜዲቴራኒያን ባህር ላይ ለአራት ቀናት ከተጓዘች በኋላ የጣልያን ማሪና ዲ ካራራ ወደብ ደረሰች።

በጆርጂያ ማሎኒ የሚመራው ቀኝ አክራሪው የጣልያን መንግሥት ፍልስተኞቹ ‘የት ይወረዱ?’ በሚል ጥያቄ ላይ መንግሥታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።

በመቀበያነት የሚመደቡት ወደቦች ፍልሰተኞቹ ለተገኙበት ሥፍራ ቅርበት ያላቸው እንዲሆኑ የአውሮፓ ረድኤት ድርጅቶች እየጠየቁ ነው።

በቅርብ በተካሄዱ ነፍስ አድን እንቅስቃሴዎች ከባህሩ ላይ ከተነሱት ፍልሰተኞች የሚበዙት የተወሰዱት እስከ 1ሺ500 ኪሎ ሜትሮች ርቀው ወደሚገኙ ወደቦች መሆኑ ተዘግቧል።

ፍልስተኞቹን ርቀው ወደሚገኙ ወደቦች ማጓጓዝ የሚገኙባቸውን የማዕከላዊ ሜዲቴራኒያን አካባቢዎች ያለ ቃፊር ጥሎ ለመሄድ፣ ብዙ መርከቦች እንዲሰባበሩና ብዙ ሞት እንዲደርስ መፍቀድ እንደሆነ በመግለፅ የረድዔት ተቋማቱ አቤቱታ እያሰሙ ነው።

ኤስኦኤስ ሜዲቴራኒያን የሚባለው የበጎ አድራጎት ድርጅት ዳይሬክተር ካርላ ሜልኪ በዚህ ጉዞ ፍልሰተኞቹን ለማትረፍ ቦታው ላይ ከመድረሳቸው በፊት አራት ተሳፋሪዎች መሞታቸውን ተናግረዋል።

የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ጉዳዮች ከፍተኛ ኮሚሽነር በዚህ በያዝነው ወር ብቻ ከሰሜን አፍሪካ ወደ አውሮፓ የሚዲቴራኒያን ባህርን ሲያቋርጡ የነበሩ 33 ሰዎች መሞታቸውን አስታውቋል። ባለፈው የአውሮፓ ዓመት 1953 ሰው ባህሩን ለማቋረጥ ሲሞክር መሞቱን ዩኤንኤችሲአር አክሎ አመልክቷል።

XS
SM
MD
LG