በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፅንስና የሚወለዱ ህፃናት ሞት ተመዝግቦባታል


ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፅንስና የሚወለዱ ህፃናት ሞት ተመዝግቦባታል
please wait

No media source currently available

0:00 0:07:27 0:00

ኢትዮጵያ ከፍተኛ የፅንስና የሚወለዱ ህፃናት ሞት ተመዝግቦባታል

የተባበሩት መንግሥታት የህፃናት ደራሽ ድርጅት /ዩኒሴፍ/ በህፃናት ሞት ላይ ያተኮሩ ሁለት ሪፖርቶችን በቅርቡ አውጥቷል።

ባለፈው የአውሮፓ የ2021 ዓ.ም. የህፃናት ሞት አኀዛዊ መረጃዎችን በገመገመበት ሪፖርቱ በዓመቱ ውስጥ በየዘጠኝ ሴኮንዱ ሁለት ህፃናት መሞታቸውንና ወደ ሁለት ሚሊየን የሚጠጋ ቁጥር ያላቸው ደግሞ አንድም ማህፀን ውስጥ ሳሉ ወይም በምጥ ወቅት እንደሚሞቱ ገልጿል።

እንዲህ ዓይነት በፅንስና በሚወለዱ ላይ ከሚደርሰው አደጋ ግማሹ የሚደርስባቸው ኢትዮጵያን ጨምሮ አምስት ሀገሮች መሆናቸውን የዩኒሴፍ ሪፖርት ይናገራል።

የአዲስ አበባ የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም የህክምና ኮሌጅ የማህፀንና የፅንስ ህክምና መምህር ፕሮፌሰር ድላየሁ በቀለ ማብራሪያ ሰጥተዋል።

ከተያያዘው ፋይል ያገኙታል፡፡

XS
SM
MD
LG