- የኮሚቴው አባላት አካሄዳቸው ሕግን የተከተለ መኾኑን ገልፀዋል
የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ጽ/ቤት አስተዳደር ጉባኤ፣ በትላንትናው ዕለት በደቡብ ምዕራብ ሸዋ - ወሊሶ ከተማ ሶዶ ዳጬ ወረዳ በሚገኘው ሀሮ በዓለ ወልድ ቤተ ክርስቲያን፣ በሕገ ወጥ መንገድ ኤጲስ ቆጶሳትን በመሾም፣ ቤተ ክርስቲያንን የማፍረስ ወንጀል ፈጽመዋል ያላቸው አካላት፥ ከደመወዝ እንዲታገዱ፣ በተቋሟ ውስጥ የሚገለገሉባቸው ቢሮዎች እና ማረፊያ ቤቶች ታሽገው በአግባቡ እንዲጠበቁ ትእዛዝ ሰጥቷል፡፡
በሦስት ሊቃነ ጳጳሳት የተካሔደውን "ሹመት" ከአስተባበሩት የኮሚቴ አባላት መካከል አንዱ መኾናቸውን የገለጹት መምህር ዳንኤል ጫላ፣ ለአሜሪካ ድምፅ በሰጡት አስተያየት፤ አካሔዳቸው ሕግን የተከተለ እንደኾነ በመጥቀስ፣ ለመሾማቸው ምክንያት ነው፤ ያሉትን አስረድተዋል፡፡
በኦሮሚያ ክልል የሚስተዋሉ የቤተ ክርስቲያን ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ሥራዎችን ለመሥራት የተቋቋመው "ወልዳ ዳንዲ አቦቲ መንፈሳዊ ማኅበር" የሕዝብ ግንኙነት ክፍል ሓለፊ መርጋ ረጋሳ በበኩላቸው፣ "ድርጊቱ የቤተ ክርስቲያንን ሕግ የጣሰ ነው"፤ በማለት ቀኖናዊ የእርምት ርምጃ እንደሚያስፈልገው ገልጸዋል። /ለዝርዝሩ ዘገባውን የያዘውን ፋይል ይመልከቱ።/