በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ዩናይትድ ስቴትስ በሶማሊያ ባደረገችው ጥቃት 30 የአልሻባብ ተዋጊዎችን ገደልኩ አለች


የሶማሊያ የፖሊስ ሰራዊት በሞቃዲሹ የከንቲባ ጽ/ቤት ፊት ለፊት
የሶማሊያ የፖሊስ ሰራዊት በሞቃዲሹ የከንቲባ ጽ/ቤት ፊት ለፊት

የዩናይትድ ስቴትስ ወታደራዊ ሃይል የሶማሊያ ወታደራዊ ሃይሎች ከባድ የሚባል ውጊያ እያደረጉ ባለበት በማዕከላዊ ሶማሊያ ጋልካድ ከተማ አቅራቢያ በፈጸመው ጥቃት 30 የሚጠጉ የአልሻባብ ተዋጊዎችን መግደሉን አፍሪኮም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

መግለጫው ‘ጥምር እራስን የመከላከል ጥቃት’ ሲል የጠራው ይኸው ተልዕኮ ከሞቃዲሹ 260 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የተፈጸመ ነው። የሶማሊያ ብሔራዊ ጦር ከመቶ በላይ በሚሆኑ የአልሻ ባብ ተዋጊዎች ከፍተኛ የሆነ ጥቃት እየተፈጸመበት እንደነበር መግለጫው ጨምሮ ገልጿል።

የአሜሪካ መንግስት የአህጉሪቱ ወታደራዊ ክንፍ የሆነው የዩናይትድ ስቴትስ አፍሪካ ኮማንድ ፖስት በጥቃቱ ሰላማዊ ሰዎች ምንም ዓይነት ጉዳትም ሆነ ሞት አላጋጠማቸውም ብሏል። ይሁን እንጂ በጥቃቱ ሶስት ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን ነው ያስታወቀው።

የሶማሊያ መንግስት እና ታጣቂ ቡድኑ የአልሻባብ ተዋጊዎች አርብ ዕለት ጋልካድ በሚገኘው የሶማሊያ የጦር ሰፈር ገብተው ቢያንስ ሰባት ወታደሮችን ገድለዋል ሲሉ አስታውቀዋል። ተዋጊዎቹ በመኪናዎች ላይ ቦምብ በማፈንዳት መሳሪያ የተኮሱ ሲሆን በኋላ ላይ መሸሻቸው ተገልጿል።

የሶማሊያ የማስታወቂያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አልሻባብ ሰባት ወታደሮችን ሲገድል የሶማሊያ ሰራዊት ደግሞ 100 የቡድኑን ተዋጊዎችን መግደላቸውን እና ‘ቴክኒካል’ በመባል የሚታወቁት መሳሪያ የጫኑ አምስት ተሽከርካሪዎች መውደማቸውን አስታውቋል።

ይሁን እንጂ ዛሬ እሁድ ከሰዓት በኋላ በተሰማ ዜና በሞቃዲሾ ከተማ ከንቲባ ዋና መሥሪያ ቤት አካባቢ አልሻባብ ተከታታይ የቦምብ ጥቃቶች የፈጸመ ሲሆን የተኩስ ልውውጥም ተደርጓል። የቡድኑ ታጣቂዎችም የከተማው ከንቲባ ጽ/ቤት መግባታቸውን ቡድኑ አስታውቋል። እስካሁን ድረስም በጥቃቱ ምን ያህል ጉዳት እንደደረሰ የታወቀ ነገር የለም።

XS
SM
MD
LG