ፊልም ለማህበረሰባዊ ንቃት ፡-ቆይታ ከጋዜጠኛ እና ፊልም ባለሙያ ማንተጋፍቶት ስለሺ ጋር
መኖሪያውን በጀርመን ሀገር ያደረገው ማንተጋፍቶት ስለሺ በብዙዎች ዘንድ ከሚታወቅበት የጋዜጠኝነት ስራው ባሻገር ዓለም አቀፋዊ ሽልማቶችን ያሸነፈ የፊልም ባለሙያ ነው ። ከዚህ በፊት "ግርታ " የተሰኘው ፊልሙ የወጣት አፍሪካዊያን የፊልም ፌስቲቫል እና ዛንዚባር ፊልም ፌስቲቫልን ጨምሮ በአራት ዓለም አቀፍ የፊልም ፌስቲቫሎች ላይ አሸናፊ ከመሆኑ ባሻገር ትልቅ ክብር የሚሰጠው ፣ "የአፍሪካ ኦስካር " ተብሎ በሚጠራው የፓን አፍሪካ የፊልም እና ቴሌቭዥን ፌስቲቫል ላይም ዕጩ ሆኗል።በተለይ ማህበረሰባዊ አንድምታ ባላቸው አጫጭር ፊልሞች ላይ ትኩረቱን ያደረገው ማንተጋፍቶት ፣በቅርቡ "የበረንዳው ንጉስ" የተሰኘ አጭር ፊልም ለተመልካች አቅርቧል ። ይህ ፊልም የካሊፎርኒያ ሲሊከን ቫሊ የአፍሪካ ፊልም ፌስቲቫልን ጨምሮ በተለያዩ ከፊልም ጋር ተያያዥ በሆኑ መድረኮች ላይ እየታየ ይገኛል። አዲሱን ፊልሙን መነሻ አድርገን ከማንተጋፍቶት ጋር ተያያዥ ሀሳቦችን መዘናል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ጃንዩወሪ 12, 2025
የጎዳና ላይ ተዳዳሪዎችን ገላ የሚያጥቡት በጎ ፈቃደኞች
-
ጃንዩወሪ 11, 2025
የወጣቶች የሱስ ተጋላጭነትና እያስከተለ ያለው የጤና ቀውስ
-
ጃንዩወሪ 11, 2025
"ልጄስ" ተከታታይ ድራማ በፓን አፍሪካን ፊልም ፌስቲቫል ላይ በሁለት ዘርፎች ተሸለመ
-
ጃንዩወሪ 11, 2025
ኢትዮጵያ የሰነደ ሙዓለ ነዋዮች ገበያን ይፋ አደረገች
-
ጃንዩወሪ 10, 2025
የጂሚ ካርተር የቀብር ሥነ ሥርዐት ተፈጸመ
-
ጃንዩወሪ 10, 2025
ስለ ሰደድ እሳቱ የትውልደ ኢትዮጵያ የሆሊውድ አካባቢ ነዋሪው ይናገራሉ