በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የካሜሩን ተፋላሚዎች ለሰላም ድርድሩ ተስማሙ


በካሜሩን የእርስ በርስ ጦርነት በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች
በካሜሩን የእርስ በርስ ጦርነት በአገር ውስጥ የተፈናቀሉ ዜጎች

የካሜሩን መንግሥት እና አንዳንድ የእንግሊዝኛ ተናጋሪ ክልል ተገንጣይ ቡድኖች የሰላም ድርድሩን ለመጀመር መስማማታቸውን ካናዳ አስታወቀች።

ተፋላሚዎቹ የተስማሙት ከ6ሺ ሰዎች በላይ የገደለውን ግጭት ለማቆም መሆኑን የካናዳ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ትናንት ዓርብ ባወጣው መግለጫ ማስታወቁን ሮይተርስ ዘግቧል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሜላኒ ጆሊ ባወጡት መግለጫ “ተፋላማዊቹ ወገኖች ሁሉን አቀፍ የሰላምና የፖለቲካ መፍትሄ በማምጣት ግጭቱን እንዲያበቃ ከሚያስችለው መፍትሄ የሚያደርሰውን ንግግር ለመጀመር መስማማታቸውን ካናዳ ታደንቃለች” ማለታቸው ተመልክቷል።

የትጥቅ ግጭቱ የተጀመረው እኤአ በ2017 ሲሆን፣ አብዛኛው ክፍል የፈረንሳይ ተናጋሪዎች በሆኑበት የማዕከላዊቷ አፍሪካ አገር፣ እንግሊዝኛ ተናጋሪ የሆኑ የካሜሩን ክልሎችን የማግለል ሁኔታ ታይቷል የሚል ቅሬታ ከተፈጠረ ወዲህ መሆኑ በዘገባው ተጠቅሷል።

በግጭቱ ለትምህርት ምንም እድል ያላገኙ 600ሺ ህጻናትን ጨምሮ ወደ 800ሺ የሚጠጉ ሰዎች መፈናቀላቸውን ካናዳ አስታውቃለች።

XS
SM
MD
LG