በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ድሬዳዋና ችግሮቿ


ድሬዳዋና ችግሮቿ
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:05 0:00

ድሬዳዋና ችግሮቿ

የድሬዳዋ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ችግሮች መንስዔ በሕገ መንግሥቱ እውቅና ያልተሰጣት መሆኑን የገለፁ አንድ የሕግ ባለሞያ ከችግሮቿ ጋር የማይገናኝ ሐሳብ ይዞ ፍላጎትን ማቀንቀን ተገቢ አለመሆኑን ገለፁ። በመሆኑ ለዚህ መፍትሔ መፈለግ እንደሚገባ የህግ ባለሞያ ጠቆሙ። “ድሬዳዋ ከተማችን ሕገ መንግሥቱ ላይ የለችም” ያሉት የሕግ ባለሞያና ጠበቃ አቶ ይትባረክ አስፋው ከተማዋ በሕገ መንግስቱ ላይ እንድትኖርና እውቅና እንዲሰጣት ጠይቀዋል። ይህንን ያሉበትንም ምክኒያት አስረድተዋል።

ባለፈው ሳምንት የፌዴሬሽን እና የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በንብረት ላይ የሚጣለውን ታክስ የባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት በተሰበሰበበት ወቅት፤ በምክር ቤቱ የድሬዳዋ አስተዳደር ተወካይ አቶ አብዱጀዋድ መሐመድ ድሬደዋን በተመለከተ ያቀረቡት ሐሳብ አነጋጋሪ ሆኖ ሰንብቷል።

አቶ አብዱጀዋድ ድሬደዋ ራሷን ችላ ክልል የማትሆን ከሆነ ወደ ሶማሌ ወይም ኦሮሚያ እንድትካለል ሕዝበ ውሳኔ እንዲደረግ ሐሳብ አቅርበው ነበር። አቶ አብዱጀዋድ ይህንን ሐሳብ ያቀረቡት ድሬዳዋ ከሌሎች ክልሎች ተለይታ ማግኘት ያልቻለቻቸውን ጥቅማጥቅሞች እንድታገኝ ከማሰብ እንጂ ሌላ የፖለቲካ አጀንዳ እንደሌላቸው ለአሜሪካ ድምጽ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ አስተዳደር የመንግስት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ደግሞ “ሕዝበ ውሳኔ ተደርጎ ወደ አንዱ ክልል መጠቃለል” የሚለውን አማራጭ አስተዳደሩ ያልመከረበት የሕዝብ ተወካዩ የግል አቋም ነው” ብሏል። /ሙሉ ዘገባውን ከተያያዘው ፋይል ይከታተሉ/

XS
SM
MD
LG