በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በጅቡቲ ስደት ላይ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ወደ ሀገራቸው ለመመልስ ተስፋ ሰንቀዋል


በጅቡቲ ስደት ላይ የሚገኙ የትግራይ ተወላጆች ወደ ሀገራቸው ለመመልስ ተስፋ ሰንቀዋል
please wait

No media source currently available

0:00 0:04:07 0:00

በኢትዮጵያ መንግሥትና በህወሓት መሃከል የተደረገውን የሰላም ሥምምነት ተከትሎ በጅቡቲ ሆልሆል መጠለያ ጣቢያ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች ወደ ሀገራቸው የመመለስ ተስፋ ማሳደራቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ።

አስተያየት ሰጪዎቹ ከሁለት ዓመት በፊት ጦርነቱ በትግራይ ሲጀመር ወደ ጅቡቲ መሰደዳቸውን ገልፀው “አሁን ግን የሰላም ሥምምነት በመደረጉ ወደ ሀገራችን ተመልሰን ከቤተሰቦቻችን ጋር መቀላቀልና በትግራይ የመልሶ ግንባታ ሂደት መሳተፍ እንፈልጋለን” ብለዋል፡፡

ሆኖም “በስምምነቱ መሰረት በትግራይ የተሟላ የመሰረታዊ አገልግሎት አለመጀመርና ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ውጭ ያሉ ኃይሎችም ከትግራይ አለመውጣታቸው ሥጋት ፈጥሮብናል” ብለዋል፡፡

የሰላም ሥምምነቱ ከተፈረመ በኋላ በትግራይ የስልክና የመብራት አገልግሎት እንዲሁም በከፊል የባንክ አገልግሎት ተጀምሯል፡፡

ባለፈው ሐሙስ ዕለት ደግሞ የአማራ ኃይሎች ከሽረና አካባቢው መውጣት መጀመራቸውን የመከላከያ ሰራዊት አስታውቋል።

XS
SM
MD
LG