በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ለሥራ ፈጣሪዎች በቂ ድጋፍ እንደማይሰጥ ወጣቶች ገለፁ


ለሥራ ፈጣሪዎች በቂ ድጋፍ እንደማይሰጥ ወጣቶች ገለፁ
please wait

No media source currently available

0:00 0:05:00 0:00

በኢትዮጵያ ተደራጅተው በሥራ ላይ የሚገኙ ሥራ ፈጣሪዎች ማኅበራት ተወካዮች በመንግሥት በቂ የሆነ ድጋፍ እንደማይደረግላቸው፤ በማኅበር የመደራጀት ዕድል ያላገኙት ደግሞ “የተመቻቸ ነገር የለም የሚሰማውም የውሸት ሪፖርት ብቻ ነው” ሲሉ አማረሩ።

የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የሥራ ስምሪትና ገበያ ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በዓመቱ ለመፍጠር ታቅዷል ካሉት 3 ነጥብ 7 ሚሊዮን የሥራ ዕድሎች ውስጥ 60 በመቶው የሚሸፈነው በጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ዘርፍ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግሥት የሚያከፋፍለው የማምረቻና መሽጫ መሬት ባይኖረውም አዲስ ለሚደራጁ ማህበራት 85 ሺህ ሄክታር መሬት ለማቅረብ ከክልል መንግሥታት ጋር መወሰኑን ገልጸዋል።

“በአገሬ ምርት እኮራለሁ ከአገር ውስጥ አምራቾች እገዛለሁ” በሚል መሪ ሐሳብ አገር አቀፍ የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች አውደ ርዕይና ባዛር ትናንት በሀዋሳ ከተማ ተከፍቷል።

XS
SM
MD
LG