በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

በማሊ በአክራሪዎች በተፈፀመ ጥቃት 14 ወታደሮች ተገደሉ


ፋይል ፎርቶ፡ የማሊ ወታደሮች በጀኔ ወንዝ አካባባቢ ቅኝት ሲያደርጉ የካቲት 28, 2020.
ፋይል ፎርቶ፡ የማሊ ወታደሮች በጀኔ ወንዝ አካባባቢ ቅኝት ሲያደርጉ የካቲት 28, 2020.

በእስላማዊ አክራሪዎች ተቀነባብሮ የተፈፀመ ነው በተባለው በማሊ ሁለት መንደሮች በደረሰ የፈንጂ ጥቃት 14 የአገሪቱ ወታደሮች መገደላቸውን የሠራዊቱ የሕዝብ ግንኙነት አስታውቋል።
የሠራዊቱ የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ሱሊማን ደምብሌ ዛሬ በሰጡት መግለጫ፣ በዚህ ሳምንት መጀመሪያ ላይ በደርሰው በዚህ ጥቃት ወቅት የማሊ ኃይሎች 30 የሚሆኑና እርሳቸው አሸባሪ ብለው የጠሯቸውን ሰዎች መግደላቸውን አስታውቀዋል።
ምዕራባዊቷ አፍሪካዊ አገር ባለፉት አሥርት ዓመታ ከአል-ቃይዳ እና ኢስላሚክ ስቴት ጋር ግንኙነት ያላቸው ቡድኖች ኢላማ ሆና ከርማለች። በሺህ የሚቆጠሩ ሰዎች በጥቃቶቹ ተገድለዋል።
የማሊ ወታደራዊ ሁንታ ጂሃዲስቶቹን መመከት እንዳቃተውና የፈረንሳይ ጦርም ከሁንታው ጋር ባለመስማማቱ ባለፈው ነሓሴ አገሪቱን ለቆ መውጣቱን የአሶስዬትድ ፕረስ ዘገባ አመልክቷል።

ከኅዳር 2014 ዓ/ም ጀምሮ የማሊ ሁንታ የሩሲያ ቅጥር ነፍሰገዳ ቡድን ከሆነው የዋግነር ቡድን ጋር ለሥራት ቢወስንም፣ ቡድኑ የአክራሪዎቹን ጥቃት ማስቆም አልቻለም ተብሏል።

XS
SM
MD
LG