በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሶማሌላንድ ወታደሮችዋን ከአወዛጋቢው ከተማ አወጣች


የሶማሌላንድና የፑንትላንድ ካርታ
የሶማሌላንድና የፑንትላንድ ካርታ

ከሶማልያ የተገነጠለችው ሶማሌላንድ ወታደሮችዋን ከሶማሌ ፑንትላንድ ጋር ከሚያወዛግባት ከላስ አኖድ ከተማ ከባለፈው ሀሙስ ጀምሮ ማውጣቷን አስታወቀች።

ፑንትላንድ ከተማዪቱ ላይ የይገባኛል ጥያቄ ቢኖራትም ከተማውን የምታስተዳድረው እኤአ በ1991 ከሶማልያ የተገነጠለችው የሶማሌላንድ መሆንዋ ተመልክቷል።

በከተማዪቱ ውስጥ አንድ የፖለቲካ ሰው በመገደላቸው ህዝባዊ ተቃውሞ የገነፈለ ሲሆን ከፖሊስ ጋር በተደረገ ግጭት በትንሹ 8 ሰዎች ሞተዋል።

የከተማዪቱ ከንቲባ አብዱራሂም አሊ በሁለቱም ወገን ያሉ ሽማግሌዎች ሁኔታዎች እንዲረጋጋ ከመከሩና የሶማሌላንድ ወታደሮችም እንዲወጡ ከተደረገ በኋላ በከተማው መረጋጋት ተመልሶ መስፈኑን ለቪኦኤ ተናግረዋል።

የሶማሌላንድ የጦር አዛዦችም ከተማውን ለቀው የወጡት ብጥብጡን ለማስቀረት መሆኑን አስታውቀዋል።

ሶማሌላንድ ከሶማልያ የበለጠ መረጋጋት የሰፈነባት ብትሆንም በአገርነት ዓለማቀፋዊ እውቅና አልተሰጣትም።

ባለፈው ሳምንት በሁለቱ ወገኖች መካከል በተካሄደ ውጊያ 15 ሰዎች መሞታቸው ተመልክቷል።

XS
SM
MD
LG