በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ኢራን ሁለት ሰዎችን በስቅላት ቀጣች


 በኢራን ዛኼዳን ከተማ ትናንት ታህሳስ 28/ 2015 የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ
በኢራን ዛኼዳን ከተማ ትናንት ታህሳስ 28/ 2015 የተካሄደ የተቃውሞ ሰልፍ

ኢራን ሁለት ሰዎችን ዛሬ ቅዳሜ በስቅላት መቅጣቷን የአገሪቱ የፍትህ ተቋም አስታወቀ።

መሀመድ ማሃዲ ካራሚ እና ሰይድ መሀመድ ሁሴን የተባሉት ሁለቱ ሰዎች የተቀጡት በፖሊስ ቁጥጥር ስር እያለች የሞተችውን ወጣት ሴት ተከትሎ በተቀሰቀሰው አገር አቀፉ አመጽ አንድ ህግ አስከባሪ ወታደር ገድለዋል በሚል ነው፡፡

የቅዳሜው የስቅላት ግድያ ፣ የተቃውሞ አመጹ ከተጀመረው ወዲህ በሞት የተቀጡ ተቃዋሚዎችን ቁጥር አራት ማድረሱ ተመልክቷል።

ተቃውሞው መነሻ ኢራን ውስጥ ከቤተሰቦችዋ ጋር ሳኬዝ ከተባለው አካባቢ ወደ ቴህራን ስትጓዝ በነበረችበት ወቅት ሂጃብን በትክክል አልተከናነብሽም በሚል እኤአ መስከረም 13/2022 በኢርሻድ አሳሾች የታሰረችው ማሻ አሚኒ በፖሊሶች ቁጥጥር ስር እንዳለች በመሞቷ ነው፡፡

የአውሮፓ ህብረት ግድያውን "አሰቃቂ" ሲል አውግዞታል፡፡

የህብረቱ የውጭ ጉዳዮች ኃላፊ ጆሴፍ ቦሬል በሰጡት መግለጫ "ይህ የኢራን ባለሥልጣናት በሲቪል ተቃዋሚዎች ላይ ጥቃት የተሞላበት አፈና የሚካሄዱ ስለመሆኑ ሌላው ምልክት ነው ብለዋል፡፡"

ባለሥልጣናቱ በተቃዋሚዎች ላይ በማስተላለፍ ላይ የሚገኘውን የሞት ቅጣት በአስቸኳይ እንዲያቆም የህብረቱ ቃል አቀባይ አሳስበዋል፡፡

XS
SM
MD
LG