ባህል፣ ትውፊት እና ታሪክን ለተተኪ ትውልድ አሻጋሪው አገልግሎት
ትውልደ-ኢትዮጵያዊያን ህጻናት እና ወጣቶች ስለ ማንነታቸው ይበልጡኑ እንዲያውቁ፣ በስነ-ምግባር እና በዕውቀት እንዲጎለብቱ ለማስቻል አልመው ከተቋቋሙ ኃይማኖታዊ መሰረት ያላቸው ተቋማት አንዱ የማህበረ ቅዱሳን የሰሜን አሜሪካ ማዕከል የተተኪ ትውልድ መርሐ-ግብር ነው። ማዕከሉ በምዕራቡ ዓለም ለሚገኙ ህጻናት እና ታዳጊዎች የቋንቋ ፣ የታሪክ እና ባህል ማስገንዘቢያ መርሐ-ግብሮችን በመዘርጋት ከመንፈሳዊ አገልግሎት ተሻግሮ ማህበረሰባዊ እና ሀገራዊ ርባና ያላቸውን እንቅስቃሴዎች ሲከውን መቆየቱ ይነገራል። ስለተወሰኑት ለማወቅ ፣ ስለመጪ ዘመን ግቦች ለመረዳት ከማዕከሉ አስተባባሪዎች መካከል ዶ/ር ህልምነህ ስንሻውን እና ወ/ሮ ህይወት ዘውዴን በእንግድነት ጋብዘናል።
የፕሮግራሙ ተከታታይ ክፍሎች
-
ፌብሩወሪ 08, 2023
ጋቢና ቪኦኤ
-
ፌብሩወሪ 07, 2023
ጋቢና ቪኦኤ
-
ፌብሩወሪ 06, 2023
ጋቢና ቪኦኤ
-
ፌብሩወሪ 05, 2023
በድባቴ እና እራስን በማጥፋት ስሜት ውስጥ ያሉ ወጣቶች ስለአዕምሮ ጤና የሚወያዩበት ቡድን
-
ፌብሩወሪ 04, 2023
ጠያቂ ፊልሞች - ቆይታ ከፊልም ባለሞያ አቤል መካሻ ጋር
-
ፌብሩወሪ 04, 2023
በሜሪላንድ ግዛት የአማርኛ ቋንቋ ትምህርት ሊጀመር ነው