በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

የሰበታና አካባቢው ዳያስፖራ ማኅበር በጎ ተግባር

የሰበታና አካባቢው ዳያስፖራ ማኅበር በጎ ተግባር
please wait

No media source currently available

0:00 0:06:59 0:00

በዴንቨር ኮሎራዶ በሰሜን አሜሪካ የሰበታና አካባቢው ዳያስፖራ ማህበር በሚል ራሳቸውን ያደራጁ ትውልደ ኢትዮጵያ አባላት በትውልድ አካባቢያቸው ሰበታ እና በሌሎች የኢትዮጵያ ከተሞች የሚገኙ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመርዳት ላይ መሆናቸውን ገልፀዋል። የማህበሩ ሀላፊዎች ከአሜሪካ ድምጽ ጋር በነበራቸው ቆይታ ከ200 አባልት በላይ ያሉት ማህበሩ በጦርነቱ ወቅት ተጎጂ የሆኑትን ጨምሮ ለኑሮ ችግረኞች የገንዘብና የቁሳቁስ ድጋፍ የሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በየዓመቱ ቁጥራቸው 700 በላይ ለሚደርሱ ተማሪዎች ሙሉ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎችን እንደሚልኩም አስረድተዋል፡፡ከማኅበሩ ምስረታ እስካሁን ወደ 400ሺ ዶላር የሚገመት እርዳታ መላካቸውንም የአመራር አባላቱ ገልጸዋል፡፡

የሰበታ አካባቢው ተወላጆች መሆናቸውን የገለጹት የአመራር አባላቱ ማህበራቸው በኢትዮጵያዊነትና ሰብአዊነት የተደራጀ መሆኑን ገልጸው የአማራና አፋር ክልልን ጨምሮ ከወለጋም የተፈናቀሉ ወገኖችን ጭምር እንደሚረዱ ተናግረዋል፡፡

የማኅበሩ አባላት በቡድን ከሚልኳቸው ሌላ በየግላቸውም የውሃ ጉዳጎዶችን በማስቆፈር የጋራ ሽንት ቤቶችን በማሰራት የሰበታ ከተማ ነዋሪዎችን በመደገፍ ላይ መሆኑ መሆኑን አቶ ፋሪስና መባ ገልጸዋል፡፡
በኮቪድ ወቅት ወደ 800 ለሚጠጉ ሰዎች የህክምና እርዳታ እንዲያገኙ ማድረጋቸውንም አስረድተዋል፡፡

ለወደፊቱ ጊዜያዊ እርዳታ ብቻ ሳይሆን ቋሚ የመሰረተ ልማት ግንባታዎችን ለማካሄድ ከሰበታ ከተማ ባለሥልጣናትና ከህዝብ ተወካዮች ጋር እየተነጋገሩ መሆኑንም የማህበሩ ኃላፊዎች ተናግረዋል፡፡

(ዝርዝሩን ከተያይዘው ፋይል ያድምጡ)

XS
SM
MD
LG