በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ጀርመን የሚገኙ የኢራን መንግሥት ተቃዋሚ ኢራናዊያን የጉዞ ማስጠንቀቂያ ተሰጣቸው


በጀርመን የኢራን ተቃዋሚዎች
በጀርመን የኢራን ተቃዋሚዎች

ጀርመን በሀገሯ የሚኖሩ የኢራንን መንግሥት የሚነቅፉ ኢራናውያን ወደዚያች ሀገር ከመጓዝ እንዲቆጠቡ አስጠንቅቃለች። የጀርመን የፌዴራሉ መንግሥት የሕገ መንግሥት አስከባሪ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ቶማስ ሀልደንዋንግ ለጀርመን ጋዜጣ በሰጡት መግለጫ "የኢራን መንግሥት ባለፉት ዓመታት የሚነቅፉት እነማን እንደሆኑ ለመለየት ሲከታተል ቆይቷል እና ሰዎቹ ወደኢራን ቢሄዱ ከባድ አደጋ ያጋጥማቸዋል" ሲሉ አሳስበዋል።

ተቃዋሚዎቹ ብቻ ሳይሆኑ ጓደኞቻቸው እና ቤተሰቦቻቸም ጭምር ተመሳሳይ አደጋ ሊደርስባቸው እንደሚችልም ባለስልጣኑ ጨምረው አስጠንቅቀዋል።

ጀርመን ውስጥ ባለፈው ጥቅምት ወር በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች የተሳተፉበትን የመሳሰሉ የኢራንን መንግሥት የሚቃወሙ ሰልፎች መካሄዳቸውን ያነሱት የጀርመኑ ባለስልጣን የኢራን መንግሥት ሰልፉን በመከታተል ተቃዋሚዎቹ እነማን እንደሆኑ ሳይለይ እንዳልቀረ አመልክተዋል።

XS
SM
MD
LG