በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሩሲያ ዩክሬን ላይ በርካታ ሚሳየሎችን አስወነጨፈች 


በሩሲያ ሚሳዬል ድብደባ ከወደሙት ሕንጻዎች አንዱ (ፎቶ ኤ.ፒ/)
በሩሲያ ሚሳዬል ድብደባ ከወደሙት ሕንጻዎች አንዱ (ፎቶ ኤ.ፒ/)

ሩሲያ በአዲሱ የአውሮፓውያን ዓመት የመጀመሪያ ቀን ዩክሬን ላይ በርካታ ሚሳየሎችን አስወንጭፋለች።

በዋና ከተማዋ ኪቭ የሚኖሩ ዩክሬናውያን ግን በረንዳቸው ላይ ቆመው የሀገራቸው ጦር የሩሲያን በደርዘን የሚቆጠሩ ሚሳዬሎች መተው ሲጥሉ በማየታቸው ደስታቸውን ሲገልጹ ውለዋል። የሚሳየል ማስጠንቀቂያ በመዲናዋ ኪቭ ቢሰማም ነዋሪዎቿ ግን “ክብር ለዩክሬን” እያሉ ሲጮሁ ተደምጠዋል።

የዩክሬን የአየር ሃይል ዕዝ በሰጠው መግለጫ ኢራን ሠር የሆኑ ሻሂድ በመባል የሚታወቁ 45 ድሮኖችን መተው ጥለዋል። 13ቱ ተመተው የወደቁት ቅዳሜ በአዲስ ዓመት ዋዜማ ሲሆን 32ቱ ደግሞ የተመቱት ዛሬ እሁድ እንደነበር ተመልክቷል።

11ኛ ወሩን በያዘው ጦርነት የሩሲያው ፕሬዝደንት ቭላድሚር ፑቲን በዩክሬን ላይ ጦርነቱን እንደ አዲስ ለመቀጠል ዝተዋል።

ፑቲን በአዲስ ዓመት መልዕክታቸው ፊታቸውን ቀጨም በማድረግ “ዋናው ጉዳይ የሩሲያ ዕጣ ፈንታ ነው፣ አባት ሀገራቸንን መከላከል የተቀደሰ ተግባራችን ነው” ብለዋል።

የዩክሬኑ ፕሬዝደንት ቮሎዲሚር ዘሌኒስኪ በበኩላቸው “እጅ ከመስጠት ወጪ አማራጭ የላችሁም ብንባልም፣ ከማሸነፍ ውጪ አማራጭ የለንም ብለናል” ሲሉ ተደምጠዋል።

XS
SM
MD
LG