ክሮዬሺያ በአዲሱ ዓመት የአውሮፓ ኅብረትን የሸንገን ቀጠና ተቀላቅላለች።
ዜጎቿ ከዚህ በኋላ የጉዞ ሰነድ ማሳየት ሳያስፈልጋቸው ወደ አውሮፓ ኅብረት አገራት መጓዝ ይችላሉ።
አራት ሚሊዮን ህዝብ ያላት ክሮዬሺያ የመገበያያ ገንዘቧንም ከዚህ ዓመት ጀምሮ ወደ ዩሮ ቀይራለች።
በእ.አ.አ 1994 ከዩጎዝላቪያ ከተለይችበት ግዜ አንስቶ “ኩና” የተሰኘውን ገንዘብ ስትጠቀም ቆይታለች።
ክሮዬሺያ የአውሮፓ ኅብረትን እ.አ.አ በ2013 ብትቀላቀልም፣ በኅብረቱ ደንብ መሠረት ግን የ ሸንገን ቀጠናውንና የዮሮ መገበያያውን በተመለከተ ዘግይታ እንድትጀምር ተደርጋለች።