በቀላሉ የመሥሪያ ማገናኛዎች

ሰሜን ኮርያ የኑክሌር መሣሪያ ምርቷን እንደምትጨምር አስታወቀች


በደቡብ ኮሪያ የሶል ከተማ አንድ የባቡር ጣቢያ መንገደኞች ባለፈው መጋቢት በሰሜን ኮሪያ የተደረገን ሚሳዬል ውንጨፋ በቴሌቭዥን ሲመለከቱ (ፎቶ ኤ.ፒ)
በደቡብ ኮሪያ የሶል ከተማ አንድ የባቡር ጣቢያ መንገደኞች ባለፈው መጋቢት በሰሜን ኮሪያ የተደረገን ሚሳዬል ውንጨፋ በቴሌቭዥን ሲመለከቱ (ፎቶ ኤ.ፒ)

ሰሜን ኮሪያ በአዲሱ ዓመት የኑክሌር መሳሪያ ምርቷን እንደምታሳድግና አዲስ የረጅም ርቀት ሚሳዬል እንደምትገነባ መሪዋ ኪም ጆንግ ኡን አስታወቁ።

ያለፈውን የፈርጆች ዓመት መጠናቀቅ አስመልክተው በገዢ ፓርቲው ስብሰባ ላይ ንግግር ያደረጉት ኪም ጆንግ ኡን፣ በአሜሪካና አጋሮቿ የሚካሄደውን የጠላትነት እንቅስቃሴ ለመቀልበስ ጠንካራ ወታደራዊ ሃይል ለመገንባት ጥረት እንዲደረግ አሳስበዋል።

“ደቡብ ኮሪያ በግልጽ የምትታይ ጠላት በመሆኗ ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ሃይሏን በከፍተኛ መጠን ለመገንባት በቂ ምክንያት ነች” ብለዋል ኪም ጆንግ ኡን።

ሰሜን ኮሪያ በቅርቡ የስለላ ሳተላይቷን እንደምታመጥቅም ኪም ጨምረው ማስታወቃቸውን የቪኦኤው ዊሊያም ጋሎ ከሶል ደቡብ ኮሪያ የላከው ዘገባ አመልክቷል።

የደቡብ ኮሪያ ጦር በምላሹ ባወጣው መግለጫ የኪም ጆንግ ኡን ንግግር ለሰላምና መረጋጋት የማይበጅ ነው ብሏል። “ሰሜን ኮሪያ የኑክሌር ሃይል ለመጠቀም ከሞከረች፣ የኪም ጆንግ ኡን አገዛዝ ፍጻሜ ይሆናል” ብሏል የደቡብ ኮሪያው ጦር መግለጫ።

ሰሜን ኮሪያ 50 የኑክሌር መሣሪያዎችን እንዲሁም እነዚህን መሸከም የሚችሉ ሚሳዬሎችን ልመገንባት በቂ አቅርቦት እንዳላት ባለሙያዎች ይናገራሉ።

XS
SM
MD
LG